በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ትረስ የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተመረጡ


ፎቶ ፋይል፦ የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሊዝ ትረስ
ፎቶ ፋይል፦ የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሊዝ ትረስ

የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሊዝ ትረስ የእንግሊዝ ወግ አጥባቂ ፓርቲ መሪና ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲሆኑ በፓርቲያቸው አባላት መመረጣቸው ተነገረ፡፡

ትረስ ከቀድሞ የእንግሊዝ የግምጃ ቤት ሹም ሪሺ ሱናክ ጋር የፓርቲውን ከፍተኛ ቦታ ለማግኘት ሲፎካከሩ መቆየታቸው ተመልክቷል፡፡

ሚኒስትሯ ትረስ ሥልጣናቸውን በሚረከቡበት ወቅት የወደቀው የእንግሊዝ ኢኮኖሚና እየናረ የመጣው የኃይል አቅርቦት ዋጋ ብርቱ ፈተና እንደሚሆናቸው ተነግሯል፡፡

ተሰናባቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን መንግሥታቸው በሙስናና ከኮቪድ-19 ፕሮቶኮል ጋር በተያያዘ ቅሌት ከተወነጀለ በኋላ ባላፈው ሀምሌ ሥልጣናቸውን በገዛ ፈቃዳቸው እንደሚለቁ አስታውቀዋል፡፡

ትረስ መንግሥታቸውን በይፋ እንዲሰመረቱ በይፋ ወደ ሚጠይቋቸው ንግሥት ኤልሳቤጥ ለመቅረብ ነገ ማክሰኞ ወደ ስኮትላንድ እንደሚጓዙ ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

XS
SM
MD
LG