በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተመድ ባለሥልጣን ሶማሊያን ጎበኙ


Somali children who fled drought-stricken areas stand by their makeshift shelters in the outskirts of Mogadishu, Sept. 3, 2022. AP
Somali children who fled drought-stricken areas stand by their makeshift shelters in the outskirts of Mogadishu, Sept. 3, 2022. AP

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ ጎዳዩች እና የአጣዳፊ ዕርዳታ ማስተባበሪያ ሃላፊ ማርትን ግሪፊትስ፣ በከፋ ሁኔታ በድርቅ በተጠቃችው ሶማሊያ የምትገኘውን የደቡብ ምዕራብ ግዛትን ጎብኝተዋል።

የቪኦኤው ሞሃመድ ዳህይሴን ከሞጋዲሹ እንደዘገበው፣ ሃላፊው በአፍሪካ ቀንድ ከሌሎቹ ሀገሮች በከፋ ሁኔታ በተጠቃችው ሶማሊያ ባደረጉት ጉብኝት ወቅት፣ ከ40 ዓመት ወዲህ የታየውን አስከፊ ድርቅ ለመቋቋም ሃገሪቱ የዓለም ድጋፍ ያሻታል ብለዋል።

በሶማሊያ ያለው ድርቅ 90 በመቶ የሚሆነውን የሃገሪቱን ክልል ሲያጠቃ፤ እስከ አሁን 1 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎችን አፈናቅሏል። 7.8 ሚሊዮን የሚሆኑት ደግሞ ሰብዓዊ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል።

ማርትን ግሪፊትስ በሶማሊያ ከደቡብ ምዕራብ ግዛት ባለስልጣኖች ጋር ከተነጋገሩ በኋላ፣ ባይዶዋ ውስጥ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ 750 ሺህ የሚሆኑ ተፈናቃዮችን ባይዶዋ ማስጠለሏ የማይታሰብ ነው ብለዋል። የአካባቢው ማህበረሰብ ተፈናቃዮቹን በመርዳት ረገድ ያደርገውን ጥረትም አድንቀዋል።

ግሪፊትስ ከጉብኝቱ በኋላ በትዊተር ባስተላለፉት መልዕክት “ለማልቀስንኳ አቅም ያጡ” ህጻናትን ማስተዋላቸውንና “ራሳቸው ህጻን የሆኑ ወላጆችን ማየታቸውን” ጽፈዋል።

“የዓለም አቀፍ ማህበረሰቡ ዝምታ ‘አደንቋሪ’ ነው” ሲሉ በስላቅ አክለዋል።

የተመድ የህጻናት አድን ድርጅቱ ዩኒሴፍ ለቪኦኤ በቅርቡ እንዳስታወቀው 500 የሚሆኑ ህጻናት በተመጣጠነ ምግብ ዕጦት ህይወታቸውን አጥተዋል።

የሶማሊያው ጠቅላይ ምኒስትር ቢሮ በበኩሉ፣ ድርቁ ከ 2 ሚሊዮን በላይ ከብቶችን እንደገደለ አስታውቋል።

XS
SM
MD
LG