በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኦባማ ኤሚ አሸነፉ


(AP Photo/Pablo Martinez Monsivais) File
(AP Photo/Pablo Martinez Monsivais) File

የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ ትናንት ማታ የኤሚ ሽልማት አሸናፊ ሆነዋል::

ኦባማ ሽልማቱን ያሸነፉት “ታላላቆቹ ብሄራዊ ፓርኮቻችን” በሚል ርዕስ በኔትፍሊክስ የተዘጋጀውን ዘጋቢ ፊልም በመተረካቸውና “ምርጥ ተራኪ” በሚል የሽልማት ምድብ አሸናፊ በመሆናቸው ነው።

የቀድሞው ፕሬዝደንት ከዚህ በፊት ሁለት መጽሕፍትን በትረካ በማቅረባቸው ሁለት የግራሚ ሽልማት አሸናፊ ሆነው ነበር።

በአምስት ክፍል የቀረበው ዘጋቢ ፊልም በዓለም ዙሪያ ያሉ ብሄራዊ ፓርኮችን የሚያሳይ ሲሆን፣ የተዘጋጀውም “ሃየር ግራውንድ” በተሰኘው የኦባማና ባለቤታቸው ሚሸል የፊልም ኩባንያ ነው።

ኦባማ የኤሚ ሽልማትን ያሸነፉ ሁለተኛው ፕሬዝደንት ናቸው።

የቀድሞ ፕሬዝደንት ድዋይት አይዘንሀወር በ1956 ልዩ የኤሚ ሽልማት አግኝተው ነበር።

ኦባማ ከዚህ በፊት “The Audacity of Hope” እና “A Promised Land” የተሰኙ መጻሕፍት በድምጽ አቅርበው የ“ምርጥ ተራኪ” ሁለት የግራሚ ሽልማቶችን ወስደዋል።

ባለቤታቸው ሚሸል ኦባማ መጽሐፋቸውን በድምጽ አቅርበው፣ ከሁለት ዓመት በፊት የግራሚ ሽልማት መውሰዳቸውን የአሶስዬትድ ፕረስ ዘገባ አስታውሷል።

XS
SM
MD
LG