በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሶማሊያ በአልሻባብ ጥቃት 22 ሰዎች ሞቱ


የዩናይትድ ስቴትስ ወታደሮች በሶማሊያ እ.ኤ.አ በ2016
የዩናይትድ ስቴትስ ወታደሮች በሶማሊያ እ.ኤ.አ በ2016

በሶማሊያ የአልሻባብ እስላማዊ ታጣቂ ቡድን በማዕከላዊ ሂራን ክልል ባደረሰው አደገኛ ጥቃት 22 ሰዎች መሞታቸውን የክልሉ ባለስልጣናት አስታወቁ።

እስላማዊ ታጣቂ ቡድኑ ዛሬ ቅዳሜ ጠዋት ወደ ሂራን ክልል ምግብ ጭኖ ይጓዝ በነበረ ልዑክ ላይ ባደርሰው ጥቃት የተነሳ የሲቪሎችን ሕይወት ሊቀጥፍ ችሏል ሲሉ ከአሜሪካ ድምጽ ጋር በስልክ የተነጋገሩት የአካባቢው ባለስልጣናት አስታውቀዋል።

ጥቃቱ የተፈፀመው በክልሉ ዋና ከተማ በለድዋይ እና በማሃስ ወረዳ መካከል ባለው ጎዳና ላይ ነው።

ባለስልጣናቱ ቡድኑ በሰብዓዊ ሉዑኩ ላይ በፈጸመው ጥቃት 17 ሰዎች የገደለ ሲሆን በተጨማሪም ተጎጆዎቹን ሊረዱ በመጡ ሲቪሎች እና ቆፋሪዎች ላይ በተቀበረ ፈንጂ በማነጣጠር አምስት ሰዎችን ገድሏል።

የሶማሊያ መንግስት ባወጣው መግለጫ ጥቃቱን አጥብቆ አውግዞ "አረመኔ እና አሳፋሪ" ሲል ገልጿል።

መንግስት ከአካባቢው ማኅበረሰብ ጎን እንደሚቆም ገልጾ ለደረሰው “አሰቃቂ” ጥቃት ጠንከር ያለ ምላሽ እንደሚሰጥ ቃል ገብቷል።

አልሻባብ ለጥቃቱ ኃላፊነቱን የወሰደ ሲሆን በጥቃቱም 20 የአካባቢውን ታጣቂዎች መግደሉን ገልጿል።

መቀመጫውን በሞቃዲሾ የሆነው የትንታኔ እና የስትራቴጂ ጥናት ማዕከል ዳይሬክተር የሆኑት አብዱራህማን ሼክ አዝሃሪ ለቪኦኤ እንደተናገሩት ‘አልሸባብ የበቀል እርምጃ እየወሰደ ነው’ ብለዋል።

አልሸባብ መንግስትን የአካባቢው ማኅበረሰቦች መንግስትን እንዳይደግፉ ለማድረግ የሚጠቀምባቸው የጋራ ቅጣት ነው ይላሉ።

XS
SM
MD
LG