በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በቻይና በኮቪድ ሳቢያ 21 ሚሊዮን ነዋሪዎች ላይ ገደብ ተጣለ


ፎቶ ፋይል፦ በደቡባዊ ምዕራብ ቻይና የምትገኘው የሼንዱ ከተማ ነዋሪዎች እአአ 2020
ፎቶ ፋይል፦ በደቡባዊ ምዕራብ ቻይና የምትገኘው የሼንዱ ከተማ ነዋሪዎች እአአ 2020

በደቡባዊ ምዕራብ ቻይና የምትገኘው የሼንዱ ከተማ ባለሥልጣናት፣ የኮቪድ 19 ወረረሽኝ መከሰትን ተከትሎ፣ 21.2 ሚሊዮን የሚሆኑት የከተማው ነዋሪዎችን እንቅስቃሴ ያገዱ ሲሆን፣ በከተማው ለአራት ቀናት የሚቆይ ምርመራ እንዲካሄድ አዘዋል፡፡

የከተማው ባለሥልጣናት ባወጡት መግለጫ ነዋሪዎች ከሀሙስ ምሽት 6 ሰዓት ጀምሮ “በመርኃ ደረጃ በየቤታቸው እንዲቆዩ” ያዘዙ ሲሆን መሠረታዊ አገልግሎት በሚሰጡ የሥራ ዘርፎች ከተሰማሩ ሰራተኞች ውጭ የተቀሩት በየቤታቸው ሆነው እንዲሰሩ ጠይቀዋል፡፡

ነዋሪዎች ከእያንዳንዱ ቤተሰብ በየቀኑ አንድ ሰው ወደ ግሮሰሪ ወይም መደብሮች መላክ የሚችሉ ሲሆን በ24 ሰዓትታ ውስጥ ከኮቪድ 19 ነጻ መሆናቸውን የሚያሳይ መረጃ ማቅረብ እንዳለባቸውም በመግለጫው ተመልክቷል፡፡

መግለጫው አክሎም ከሀሙስ እስከ እሁድ ባለው ጊዜ ምርመራ ስለሚካሄድ “በጣም የግድ” ካልሆነ በቀር ነዋሪዎቹ ከተማዪቱን ለቀው እንዳይወጡ አሳስቧል።

XS
SM
MD
LG