በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ትዊተር ማሻሻያ አደረገ


የማኅበራዊ መገናኛ መድረክ ትዊተር
የማኅበራዊ መገናኛ መድረክ ትዊተር

የማኅበራዊ መገናኛ መድረኩ ትዊተር፣ ተጠቃሚዎቹ መልዕክቶቻቸውን ከሰደዱ በኋላ መልሰው ማስተካከል ወይም ኤዲት ማድረግ የሚችሉበትን አገልግሎት ሰርቶ፣ የውስጥ ፍተሻ እያደረገ መሆኑን አስታወቀ፡፡

በመጭው ሳምንታት ሲጠበቅ የቆየውን አገልግሎት፣ ለከፋይ ደንበኞቹ ሥራ ላይ እንደሚያውላቸውም የማኅበራዊ መገናኛ መድረኩ ድርጅት ዛሬ ሐሙስ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

የትዊተር ተጠቃሚዎች መልዕክቶቻቸውን አንዴ ካተሙ በኋላ፣ የሆሄያት ግድፈትንም ሆነ አንዳንድ ስህተቶችን ማቃናት የሚያስችላቸው አገልግሎት ለረጅም ጊዜ ሲጠይቁ መቆየታቸው ተገልጿል፡፡

ካሁን በኋላ ግን ተገልጋዮቹ የትዊት መልዕክታቸውን ባተሙ ወይም ባስተላለፉ በ30 ደቂቃ ውስጥ “ለጥቂት ጊዚያት” መላልሰው ማስተካከል የሚችሉ መሆኑን ድርጅቱ አስታውቋል፡፡

XS
SM
MD
LG