በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በህንድ በደረሰ የጎርፍ እና መሬት መንሸራተት አደጋ 40 ሰዎች ሞቱ


በህንድ ሀማቻል ፕሬዴሽ ግዛት በሚገኘው ዳርማሳላ ከተማ የመሬት መንሸራተት መንገዶችን በመዝጋቱ ሞተረናው ጭቃውንና ፍርስራሾችን ለማለፍ ሲሞክር - Aug. 21, 2022.
በህንድ ሀማቻል ፕሬዴሽ ግዛት በሚገኘው ዳርማሳላ ከተማ የመሬት መንሸራተት መንገዶችን በመዝጋቱ ሞተረናው ጭቃውንና ፍርስራሾችን ለማለፍ ሲሞክር - Aug. 21, 2022.

ላለፉት ሶስት ቀናት በህንድ ሰሜናዊ ክፍል በደረሰ የጎርፍ እና መሬት መንሸራተት አደጋ ቢያንስ 40 ሰዎች መገደላቸውን እና ሌሎች በርካታ ሰዎች እስካሁን የደረሱበት እንዳልታወቀ ባለስልጣናት አስታወቁ።


ሀማቻል ፕሬዴሽ እና ኡታራካንድ በተሰኙ የህንድ ከተሞች በመቶዎች የሚቆጠሩ መንደሮችን ያጥለቀለቀው ዝናብ የጭቃ ቤቶችን ጠራርጎ ይወሰደ ሲሆን፣ መንገዶችን እና ድልድዮችን አውድሟል። የሀገሪቱ የአየር ትምበያ ሀላፊዎች እንዳሉት ከፍተኛ የሆነው ዝናብ ለሚቀጥሉት ሁለት ቀናትም መጣሉን ይቀጥላል።

በሀማቻል ፕሬዴሽ ላለፉት ሶስት ቀናት የቀጠለው የመሬት መንሸራተት እና የጎርፍ አደጋ ቢያንስ 36 ሰዎችን መግደሉ ሲታወቅ ቤታቸው በጎርፍ የተወሰደባቸው በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በርዳታ መስጫ ጣቢያዎች ውስጥ ተጠልለዋል።

በተመሳሳይ በኡታራካንድ የጣለው ዝናብ አራት ሰዎችን የገደለ ሲሆን 13 ሰዎች እስካሁን የደረሱበት አልታወቀም።

XS
SM
MD
LG