በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሌላ የዩናይትድ ስቴትስ ባለስልጣን ታይዋንን ጎበኙ 


ፋይል - የኢንዲያና ግዛት አስተዳዳሪ ኤሪክ ሆልከም 
ፋይል - የኢንዲያና ግዛት አስተዳዳሪ ኤሪክ ሆልከም 

የዩናይትድ ስቴትስ ክፍለግዛት የሆነችው ኢንዲያና አስተዳዳሪ፣ ቻይና ወደ ታይዋን ጉዞ እንዳይደረግ የምታደርገውን ግፊት በመናቅ ወደ ታይዋን ዋና ከተማ ቴይፒ ጉዞ ያደረጉ ሌላኛው የዩናይትድ ስቴትስ ባለስልጣን ሆነዋል።


ቻይና፣ ከቴይፒ መንግስት ተቃውሞ ውጪ በዲሞክራሲ መንገድ የተመረጠ አስተዳዳሪ ያላትን ታይዋንን የግዛቷ አካል አድርጋ የምትቆጥራት ሲሆን፣ በቅርቡ የዩናይትድ ስቴትስ ምክርቤት አፈጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ በቴይፒ የሁለት ቀን ጉብኝት ማድረጋቸውን ተከትሎ በታይዋን አቅራቢያ የጦር ልምምድ ስታደርግ ቆይታለች።


ባለፈው ሳምንትም የዩናይትድ ስቴትስ ህግ አውጪዎችን የያዘ ሁለተኛ ቡድን ወደ ታይዋን ተጉዞ ነበር።

የኢንዲያና አስተዳዳሪ ኤሪክ ሆልከም በትዊተር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ ከሁለት አመት በፊት የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ከተነሳ ወዲህ ታይዋንን የጎበኙ የመጀመሪያው የዩናይትድ ስቴትስ ግዛት አስተዳዳሪ መሆናቸውን ገልፀው በታይዋን እና ደቡብ ኮሪያ የሚያደርጉት ጉዞ አላማ የኢኮኖሚ ልማት መሆኑን አስታውቀዋል።

የኢንዲያና አስተዳዳሪውን ጉዞ አስመልክቶ ቻይና ያለችው ነገር ባይኖርም በታይዋን አካባቢ የምታደርገውን ወታደራዊ ልምምድ ግን እንደቀጠለች ናት።

XS
SM
MD
LG