በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ናይጄሪያ የ52 ሚዲያዎችን ፈቃድ ልትሰርዝ ነው


አቡጃ - ናይጄሪያ 
አቡጃ - ናይጄሪያ 

የናይጄሪያ ብሮድካስት ባለስልጣን የ52 ዜና ማሰራጫ ጣቢያዎችን ፈቃድ ሊሰርዝ መሆኑን አርብ እለት አስታውቋል። ባለስልጣኑ ፈቃዱን የሚሰርዘው የሚጠበቅባቸውን ክፍያ ባለመፈፀማቸው ነው ቢልም የሀገሪቱ ጋዜጠኞች ማህበር ግን "ያለማገናዘብ የተወሰደ ርምጃ" ነው ሲል ውሳኔውን አጣጥሎታል።


ውሳኔውን ይፋ ያደረገው የናይጄሪያ ብሄራዊ ብሮድካስቲንግ ኮሚሽን፣ የሚዲያ ተቋማቱ በአጠቃላይ 6.2 የአሜሪካን ዶላር እዳ እንዳለባቸው እና ክፍያቸውን የመፈፀሚያ ግዜ እንደተሰጣቸው ገልጾ፣ ክፍያውን በተሰጠው ግዜ የማይፈፅሙ በ24 ሰዓት ውስጥ እንደሚዘጉ ገልጿል።


ውሳኔውን 'በችኮላ የተፈፀመ' እና 'ያለማገናዘበ የተወሰደ ርምጃ'
ሲል የገልፀው የናይጄሪያ የጋዜጠኞች ማህበር በበኩሉ፣ ኮሚሽኑ በአሁኑ ወቅት ናይጄሪያ ውስጥ ያለውን የኢኮኖሚ ሁኔታ ያላገናዘበ ርምጃ መውሰዱን እና እና ክፍያዎቹ እ.አ.አ ከ2015 ጀምሮ ሲንከባለሉ የቆዩ መሆናቸውን ባወጣው መግለጫ አመልክቷል።

"በሀገሪቱ ውስጥ ያለውን የፀጥታ ሁኔታ ግምት ውስጥ ባላስገባ መልኩ በብሮድካት ሚዲያ ጣቢያዎች ላይ ከፍተኛ መጠን ያለው አፈና ማድረግ ትክክል አልመሆኑን እናስጠነቅቃለን። በዚህ ወቅት ይህን ያክል ሚዲያ በአንድ ግዜ መዝጋት የሚያስከትለውን መጥፎ ሁኔታ ልንቋቋመው የማንችለው ነው" ሲልም ማህበሩ ምላሽ ሰጥቷል።

XS
SM
MD
LG