በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሞቃዲሾ ሆቴል ላይ ለደረሰው ጥቃት አልሻባብ ኃላፊነቱን ወሰደ 


ፖሊስ እና የጦር ሰራዊት አባላት፣ ከአልቃይዳ ጋር ቁርኝት ያለው አልሻባብ ታጣቂ ቡድን በሞቃዲሾ ያደረሰውን ጥቃት ሲያጣሩ Aug. 21, 2022.
ፖሊስ እና የጦር ሰራዊት አባላት፣ ከአልቃይዳ ጋር ቁርኝት ያለው አልሻባብ ታጣቂ ቡድን በሞቃዲሾ ያደረሰውን ጥቃት ሲያጣሩ Aug. 21, 2022.

ከአልቃይዳ ጋር ቁርኝት ያለው የአልሻባብ ታጣቂ ቡድን ሶማሊያ በሚገኝ ሆቴል ላይ ያካሄደው ከበባ፣ የፀጥታ ኃይሎች ባደረጉት 30 ሰዓታት የፈጀ ወታደራዊ ምላሽ መጠናቀቁን የሶማሊያ ፌደራል ፖሊስ ዛሬ አስታወቀ። ባለስልጣናቱ በጥቃቱ ከ20 ሰዎች በላይ መገደላቸውን እና 40 ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን ያታወቁ ሲሆን ከአርብ ማታ ጀምሮ እስከ ቅዳሜ በታጣቂዎቹ እና በፀጥታ አካላት መካከል በተካሄደው ከፍተኛ ውጊያ የሆቴሉ አብዛኛው ክፍል መውደሙን ቢቢሲ ዘግቧል።


የሶማሌ ፖሊስ አዛዥ ጀነራል አብዲ ሀሰን ዛሬ በሀገሪቱ ዋና መዲና ሞቃዲሾ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የፀጥታ ኃይሎች ዋና አላማ "አልሻባብ ጥቃት ባደረሰበት ሀያት ሆቴል ውስጥ ታግተው የነበሩ ንፁሃን ዜጎችን ማዳን ነበር" ያሉ ሲሆን ከበባው ትላንት እኩለ ለሊት ሲጠናቀቅ ሴቶች እና ህፃናትን ጨምሮ ከ106 በላይ ሰዎች ማትረፋቸውን ገልፀዋል።

ሀያት ሆቴል ከፍተኛ ደረጃ ያለው እና በአብዛኛው በመንግስት ባለስልጣናት እና ከውጪ የሚመጡ ሰዎች የሚዘወተር ሲሆን በጥቃቱ ከተገደሉ እና ጉዳት ከደረሰባቸው መካከል ነጋዴዎች እና አረጋውያን ይገኙበታል። ከሆቴሉ ባለቤቶች መካከል አንደኛው፣ አብድራህማን ኢማንም በጥቃቱ መገደላቸውን ዘመዶቻቸው አስታውቀዋል።

XS
SM
MD
LG