በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሶማሌና አፋር ክልሎች ወሰን ላይ በተነሳ ግጭት ነዋሪዎች ተፈናቀሉ


ሶማሌና አፋር ክልሎች ወሰን ላይ በተነሳ ግጭት ነዋሪዎች ተፈናቀሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:47 0:00

ሶማሌና አፋር ክልሎች ወሰን ላይ በተነሳ ግጭት ነዋሪዎች ተፈናቀሉ

ሶማሌና አፋር ክልሎችን ለብዙ ዓመታት ሲያወዛግቡ በነበሩ ሦስት ወሰን አጋሪ ከተሞች ውስጥ በተቀሰቀሰ ግጭት ነዋሪዎች ተፈናቀሉ።

በሶማሌ ክልል በኩል የሚገኙ ነዋሪዎች “የአፋር ክልል ልዩ ኃይሎች ድንገት ፈፅመውታል ባሉት ጥቃት ሰዎች እንደተገደሉ እና ነዋሪዎች እንደተፈናቀሉ” ገልፀዋል።

የውዝግብ መንስኤ የሆኑት አደይቱ፣ ገርበ ኢሴ (ገዳማይቱ) እና ኡንዱፎ በአፋር ክልል ልዩ ኃይል ቁጥጥር ሥር መሆናቸውን ጨምረው ተናግረዋል።

በአፋር በኩል ደግሞ የአካባቢው ነዋሪና የክልሉ የቀድሞ አመራር አባል አቶ አብዱ አሊ “ከሶማሌ ክልል በኩል ተፈፅሞብናል ያሉት ጥቃት የአፀፋ ምላሽ እንዲሰጡ እንዳስገደዳቸው” ተናግረዋል።

በጥቃቱ የተፈናቀሉት ስድሣ ሺህ ሰዎች ለችግር መዳረጋቸውን የሶማሌ ክልል ገልፆ የፌደራል መንግሥቱን ድጋፍ ጠይቋል።

ከፌዴራል መንግሥት ምላሽ ማግኘት አልቻልንም።

XS
SM
MD
LG