በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስ ም/ቤት ልዑካን ቡድን ከአዲሱ የኬንያ ፕሬዚዳንት ጋር ተገናኙ


የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ልዑካን ቡድን ከአዲሱ የኬንያ ፕሬዚዳንት ጋር ተገናኙ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:18 0:00

የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ልዑካን ቡድን ከአዲሱ የኬንያ ፕሬዚዳንት ጋር ተገናኙ

የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ልዑካን ቡድን ከኬንያው አዲስ ተመራጭ ፕሬዚዳንት እና የምርጫ ውጤቱን ተቃውመው ፍርድ ቤት ክስ ለመመስረት እየተዘጋጁ ከሚገኙት ተቃዋሚ መሪ ጋር ለመነጋገር በምስራቅ አፍሪካ የተረጋጋ ዲሞክራሲ እንዳላት በሚነገርላት ኬንያ ገብተዋል።

ልዑካኑ አዲስ ከተመረጡት ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ጋር ዛሬ የተገናኙ መሆናቸውን ሩቶ በትዊተር ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት አስታውቀዋል።

በሴናተር ክሪስ ኩንስ የተመራው ልዑካን ቡድን ባለፈው ሳምንት በሰላማዊ መንገድ ምርጫው ከተጠናቀቀ ወዲህ ድምፃቸው ያልተሰማውን ተሰናባቹን የኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታንም እንደሚያገኙ በኬንያ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር የሆኑት ሜግ ዋይትማን ተናግረዋል።

ዊሊያም ሩቶ የኬንያታ ምክትል ፕሬዚዳንት ቢሆኑም ከዓመት በፊት በሁለቱ ሃካከል ቅራኔ በመፈጠሩ ኬንያታ በምርጫው ድጋፋቸውን የሰጡት የረጅም ግዜ ተቀናቃኛቸው ለነበሩት ራይላ ኦዲንጋ ነው።

አዲንጋ ምርጫውን ተከትሎ ባደረጉት ንግግር የምርጫውን ውጤት እንደማይቀበሉት እና ሕገ መንግሥታዊ እና ሌሎች ሕጋዊ አማራጮችን እየተመለከቱ መሆኑን ገልፀዋል። ጉዳዩን ወደ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ለመውሰድ የምርጫ ውጤቱ ይፋ ከተደረገበት ቀን አንስቶ ባለው አንድ ሳምንት ግዜ ውስጥ ክስ መመስረት ያለባቸው ሲሆን ፍርድ ቤቱ በ14 ቀናት ውስጥ ብይን ይሰጣል። ያ እሰከሚሆን ግን ኦዲንጋ ደጋፊዎቻቸው ተረጋግተው እንዲጠብቁም አሳስበዋል።

የኬንያ የምርጫ ኮሚሽን ሰኞ እለት ውጤቱን ይፋ ከማድረጉ ጥቂት ደቂቃዎች ቀደም ብሎ ኮሚሽነሮቹ በመጥፎ ተግባር ተወነጃጅለው በተፈጠረ ትርምስ በይፋ ተከፋፍለዋል። የሰኞውን የምርጫ ውጤት የተቃወሙትን አራት ኮሚሽነሮች ኬንያታ ሹመት የሰጧቸው ባለፈው አመት ነበር።

የአሜሪካ ምክር ቤት የውጭ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ አባላትን ያካተተው ልዑካን ቡድን ከኬንያ ቀደም ብሎ ኬፕ ቨርዲን እና ሞዛምቢክን የጎበኘ ሲሆን ወደ ሩዋንዳም አቅንቶ ከኮንጎ ጋር ስላለው ውጥረት እና የመብት ጥሰቶች ዙሪያ እንደሚነጋገሩ ይጠበቃል።

XS
SM
MD
LG