በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ወደ አዲስ አበባና ወደ ኦሮምያ ልዩ ዞን የተካለሉ አካባቢዎች


የፌዴራል መንግሥት፣ የኦሮምያ ክልላዊ መንግሥትና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባለሥልጣናት፣ ዮሐንስ መኮንን/ኢዜማ/
የፌዴራል መንግሥት፣ የኦሮምያ ክልላዊ መንግሥትና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባለሥልጣናት፣ ዮሐንስ መኮንን/ኢዜማ/

በአዲስ አበባ አስተዳደር የተገነቡ የጋራ መኖሪያ ቤቶች የሚገኙባቸው ኮዬ ፈጬ፤ ቱሉ ዲምቱ በከፊልና ጀሞ ቁጥር ሁለት ወደ ኦሮምያ ልዩ ዞን መካለላቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ዛሬ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ ዛሬ ባሰፈሩት ፅሁፍ ገልፀዋል።

በኦሮምያ ክልል የተገነቡት የቆጣሪ ኮንዶሚኒየም ወይም ለቡ አካባቢ ፉሪ ሃናና የኦሮምያ ኮንዶሚኒየሞችን ጨምሮ እስከ ቀርሳ ወንዝ ያለው አካባቢ ወደ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እንዲካለል ስምምነት ላይ መደረሱንም ከንቲባዋ አመልክተዋል።

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ከቀናት በፊት ባወጣው መግለጫ ውሳኔውን ተቃውሟል።

የፓርቲው ምክትል መሪ ዮሐንስ መኮንን ለቪኦኤ በሰጡት ማብራሪያ "ውሳኔው ወቅቱን ያልጠበቀና ሕዝብም ያልተወያየበት ነው" ብለዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያግኙ።

ወደ አዲስ አበባና ወደ ኦሮምያ ልዩ ዞን የተካለሉ አካባቢዎች
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:29 0:00
XS
SM
MD
LG