ሱዳን ውስጥ እየጣለ ያለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ የሞተው ሰው ቁጥር 66 መድረሱን አንድ የሃገሪቱ ባለሥልጣን አስታወቁ።
ሌሎች ቢያንስ 28 ሰዎች በጎርፉ መጎዳታቸውን የሱዳን የዜጎች ደኅንነት ጥበቃ ብሄራዊ ምክር ቤት ባለሥልጣን ገልጠዋል።
ሃያ አራት ሺህ መኖሪያ ቤቶችና ሁለት የመንግሥት መሥሪያ ቤት ህንፃዎች ላይ ከባድ ጉዳት መድረሱን ወይም ሙሉ በሙሉ መውደማቸውን ባለሥልጣኑ አመልክተዋል።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ ደግሞ 238 የጤና ተቋማት መጥለቅለቃቸውን አስታውቋል።