ማሊ ውስጥ በቅጥር ተዋጊነት ተወንጅለው የታሰሩ አርባ ዘጠኝ የአይቮሪ ኮስት ወታደሮች የአገር ፀጥታ በማደፍረስ ወንጀል ክሥ ተመሠረተባቸው።
ይህንኑ ከትናንት በስተያ፤ ዕሁድ ያስታወቁት የማሊ ፀረ-ሽብር ልዩ ግብረ ኃይል አቃቤ ህግ ናቸው።
አይቮሪ ኮስት ባለፈው ሐምሌ መጀመሪያ ማሊ ዋና ከተማ ባማኮ አይሮፕላን ጣቢያ ላይ ከተያዙበት ጊዜ አንስቶ ታስረው የሚገኙት ወታደሮቿ እንዲለቀቁ ስትጠይቅ ቆይታለች።