በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኬንያ ምርጫ አስፈፃሚው ሞቶ ተገኘ


የኬንያ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ውጤት መገለጹን ተከትሎ የተቃውሞ ሁከት በናይሮቢ፣ ኬንያ እአአ 15/2022
የኬንያ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ውጤት መገለጹን ተከትሎ የተቃውሞ ሁከት በናይሮቢ፣ ኬንያ እአአ 15/2022

ባለፈው ሳምንት የደረሰበት መጥፋቱ የተነገረ የኬንያ ምርጫ አስፈፃሚ ሞቶ መገኘቱን የሃገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘገቡ። በናይሮቢ ምርጫ አስፈፃሚ የነበረውን የ53 ዓመቱን ዳንኤል ሙሲኦካን አስከሬን ከናይሮቢ ወጣ ብሎ ኪሎምቤሮ በተባለ ጫካ ውስጥ እረኞች እንዳገኙት ታውቋል።

ሙሲኦካ የተገደለው ሌላ ቦታ ሊሆን እንደሚችልና አስከሬኑን የተገኘበት ጫካ ውስጥ ሳይጥሉት እንዳልቀረ የአካባቢው ፖሊስ ተናግሯል።

ግለሰቡ ባለፈው ሃሙስ ይሠራበት ከነበረው የናይሮቢ ድምፅ መቁጠሪያ ማዕከል መሰወሩን የምርጫ ኮሚሽኑ ባለሥልጣናት ትናንት አስታውቀው ነበር።

የዛሬ አምስት ዓመት በተደረገው ምርጫም ክሪስ ሙሳዶ የተባለ የምርጫ ኮሚሽኑ የመረጃ ቴክኖሎጂ ባለሙያ መገደሉ ይታወሳል።

XS
SM
MD
LG