በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጨው እጥረት በኢትዮጵያ


የጨው እጥረት በኢትዮጵያ
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:03 0:00

የጨው እጥረት በኢትዮጵያ

ኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ የጨው ምርት ክምችት ቢኖርም ገበያው ላይ እጥረት መፈጠሩን ነጋዴዎችና ተጠቃሚዎች ይናገራሉ።

በአፋር ክልል ከፍተኛ የጨው ምርት ክምችት መኖሩም የገለፀው የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር በክልሉ አፍዴራ ላይ ብቻ 40 ሚሊዮን ኩንታል ጨው ተመርቶ ወደገበያ አለመግባቱን አረጋግጧል፡፡

መንግስት በደለደለላቸው ኮታ መሰረተ ምርታቸውን ለመግዛት ውል የገባው ድርጅት ቃሉን ባለማክበሩ ለኪስራ ጭምር መዳረጋቸውን ጨው አምራቾቹ ይናገራሉ።

ጨው ላይ አዮዲን ጨምረው፣ ፈጭተውና በመጠን አሽገው ለሸማቹ የሚያቀርቡ ፋብሪካዎችም ደግሞ በጨው እጥረት ምክንያት ስራ ማቆማቸውን ለአሜሪካ ድምጽ ገልጸዋል፡፡

በምርት እጥረቱ ምክንያት ግለሰብ ሸማቾች ከ3 እስከ አምስት ብር የሚገዙትን አንድ ኪሎ ጨው እስከ 40 ብር አውጥተው ለመሸመት መገደዳቸውን ያስታወቁ ሲሆን ጨውን በግብአትነት የሚጠቀሙ ኢንዱስትሪዎችም የችግሩ ሰለባ እየሆኑ ነው ተብሏል፡፡

/ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/

XS
SM
MD
LG