በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በክሪምያ የሩሲያ ጦር ሰፈር ስለደረሰው ጉዳት፤ የሳተላይት ምስሎች


የሳይተላይት ምስሎች
የሳይተላይት ምስሎች

ክሪሚያ በሚገኘው የሩሲያ የአየር ኃይል መደብ ላይ ከፍተኛ ውድመት መድረሱን ዛሬ ሀሙስ የተለቀቁ የሳይተላይት ምስሎች አሳይተዋል።

ምስሎቹ ኪዪቭ የጦርነቱን መልክ ሊቀይሩና ዒላማዎቻቸውን በረጅም ርቀት የመምታት አቅም ያላቸው ሚሳይሎችን ስለማግኝቷ ጠቋሚ መሆናቸው ተመልክቷል።

ፕላኔት ላብስ የሚባል ገለልተኛ የሳይተላይት ድርጅት በሩሲያው ሳኪ አየር ኃይል ሠፈር ውስጥ የሚገኙ ህንፃዎች በትክክል ተነጥለው የተመቱባቸው ሦስት ተመሳሳይ ጉድጓዶችን አሳይቷ።

በደቡብ ምዕራብ ክሪሚያ የባህር ዳርቻ የሚገኝ የጦር ሠፈር ከፍተኛ ቃጠሎ እንደደረሰበትና በሥፍራው የነበሩ ቢያንስ ስምንት የጦር ጄቶች መውደማቸውን በግልጽ ማየት እንደሚቻል ሮይተርስ ዘግቧል።

ሩሲያ በጄቶቹ ላይ ምንም ጉዳት አለመድረሱን ገልፃ ባለፈው ማክሰኞ በጦር ሠፈሩ ላይ የታየው ፍንዳታ በድንገተኛ አደጋ የተፈጠረ መሆኑን አመልክታለች።

ዩክሬን ለጥቃቱ ኃላፊነቱን በይፋ አልወሰደችም። ጥቃቱ ስለተፈፀመበት ሁኔታም ምንም አስተያየት አልሰጠችም።

ምዕራባውያን ወታደራዊ ጠበብት ግን “የደረሰው የውድመት መጠንና የዒላማው በትክክል መመታት ትልቅ የሆነ አዲስ አቅምና ትኩረት የሚስብ ነገር መኖሩን ያመላክታል ማለታቸውን ሮይተርስ አክሎ ጠቁሟል።

XS
SM
MD
LG