በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጉራጌ ዞን ም/ቤት በክላስተር ለመደራጀት የቀረበውን የውሳኔ ሐሳብ ውድቅ አደረገ


የጉራጌ ዞን ምክር ቤት
የጉራጌ ዞን ምክር ቤት

ይቀራረባሉ የተባሉ ዞኖች ወረዳዎች ተጣምረው ከሌሎች የአስተዳደር መዋቅሮች ጋር በክላስተር እንዲደራጁ የቀረበውን የውሳኔ ሐሳብ የጉራጌ ዞን ምክር ቤት በአብላጫ ድምጽ ውድቅ አደረገው።

ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ በዋና አስተዳዳሪው አቶ መሐመድ ጀማል በኩል የቀረበው ምክረ ሐሳብ ውይይት ተደርጎበት በ40 ድጋፍ እና በ52 ተቃውሞ ውድቅ መደረጉን የዞኑ ኮምዩኒኬሽንስ ቢሮ በፌስቡክ ገፁ ላይ ባሰፈረው ጹሑፍ ይፋ አድርጓል።

ዋና አስተዳዳሪው አቶ መሐመድ ያቀረቡት ሐሳብ በገዢው ብልጽግና ፓርቲ የተዘጋጀውና ሌሎች ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች ሰሞኑን ያፀደቁት የክላስተር የክልል አደረጃጀት ሐሳብ ነው።

በሁለት ተከፍለው እንደ አዲስ ይደራጃሉ ከተባሉት 11 ዞኖች እና ስድስት ልዩ ወረዳዎች ውስጥ ሁሉም ውሳኔውን ተቀብለው ማፅደቃቸውን መዘገባችን ይታወሳል። ጉራጌ ዞን ውሳኔውን ባለመቀበል በምክር ቤቱ ሲያፀድቅም የመጀመሪያው ነው።

/አድማጮች በዚህ ጉዳይ ላይ ሰፋ ያለ ዘገባ ይዘን እንመለሳለን/

XS
SM
MD
LG