በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኬንያውያን የፕሬዝዳንት ምርጫውን ውጤት እየተጠባበቁ ነው


በኬንያ ናይሮቢ በሚገኘው የምርጫ ውጤት ማካመቻ ውስጥ የፀጥታ አባል ቆሞ ይታያል - ረቡዕ፣ ኦገስት 10, 2022
በኬንያ ናይሮቢ በሚገኘው የምርጫ ውጤት ማካመቻ ውስጥ የፀጥታ አባል ቆሞ ይታያል - ረቡዕ፣ ኦገስት 10, 2022

ኬንያውያን ማክሰኞ እለት በተረጋጋ ሁኔታ የተካሄደውና ከተለመደው ያነሰ መራጭ ተሳትፎበታል የተባለውን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ውጤት እየተጠባበቁ ነው።

ከስልጣን ከሚሰናበቱት ፕሬዝዳንት እና የቀድሞ ተቀናቃኛቸው ኡሁሩ ኬንያታ ድጋፍ የተቸራቸው፣ ለረጅም ግዜ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ሆነው ለመሩት ራይላ ኦዲንጋም ፕሬዝዳንት ለመሆን ይህ የመጨረሻ ሙከራቸው ሊሆን ይችላል። ተቀናቃኛቸው የፕሬዝዳንት ምክትል የነበሩት እና ከፕሬዝዳንቱ ጋር ቅራኔ ውስጥ የገቡት ዊሊያም ሩቶ ናቸው።

በከፍተኛ ዋጋ ጭማሪ እና በሀገሪቱ በተንሰራፋው ሙስና ምክንያት የተማረሩት መራጮች ግን በዚህ ምርጫ እውነተኛ ለውጥ ይመጣል ብለው ብዙም ተስፋ እንደማያደርጉ ተናግረዋል።

በኬንያ የተካሄደውን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ተከትሎ የኬንያ ቴሌቭዥን ያስተላለፈው የቅድሚያ ውጤት በምክትል ፕሬዝዳንቱ ዊሊያም ሩቶ እና ለረጅም ግዜ የተቃዋሚ መሪ የነበሩት እና አሁን በገዢው ፓርቲ በተደገፉት ራይላ ኦዲንጋ መሀከል ያለው ልዩነት እጅግ ጠባብ መሆኑን ያሳያል።

በዚህ ምክንያት ነሐሴ 10፣ 2014 ውጤት እንዲያሳውቅ በሚጠበቅበት ገለልተኛው የምርጫ ኮሚሽን ላይ ጫናው እያየለበት ሲሆን ሰራተኞቹ ድምፅ ቆጠራ ለማካሄድ እና ይጭበረበራል የሚለውን ፍርሃት ለማስወገድ፣ ታዛቢዎች ባሉበት ለሊቱን ሙሉ ቆጠራ ሲያካሂዱ አድረዋል።

የኮሚሽኑ ሊቀመንበር ዋፉላ ቻቡካቲ ምሽቱን በሰጡት መግለጫም "ይሄንን ጥብቅ ክትትል የሚያስፈልገው ስራ እንስክናካሂድ እና በተቻለ መጠን በፍጥነት ለመጨረስ እየደከምን ባለበት ወቅት ኬንያኖች በትዕግስት እንዲጠባበቁ እንጠይቃለን" ሲሉ ጥሪ አስተላልፈዋል።

ለፕሬዝዳንትነት የሚካከሩት ምክትል ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ እና ራይላ ኦዲንጋ በጣም ተቀራራቢ የሆነ ውጤት ያላቸው መሆኑን የኬንያ ሚዲያ በሰንጠረዥ አስቀምጦ ያወጣው ውጤት ያሳየ ሲሆን አሸናፊው ከ50 ከመቶ በላይ የሆነ ድምፅ ማግኘት ይጠበቅበታል።

የሚዲያውን ውጤት የተከታተሉ ምሁራን በሰጡት አስተያየት ግን፣ በውጤቱ ላይ ስህተት እንዳገኙበት ገልፀው፣ ይፋዊ ውጤት አለመሆኑን በማስገንዘብ አስጠንቅቀዋል።

የምርጫ ኮሚሽኑ ውጤቱን በአንድ ሳምንት ውስጥ እንዲያሳውቅ የሚጠበቅበት ሲሆን ምናልባት አሸናፊው እስከ ሪቡዕ ባለው ጌዜ ሊታወቅ የሚል ግምት አለ። የምርጫ ኮሚሽኑ ከመላው ሀገሪቱ የሚመጡትን ውጤቶች ማጣራት የሚጠበቅበት ሲሆን ከ46 ሺህ በላይ ከሚሆኑ የምርጫ ጣቢያዎች ከተሰበሰቡት ውጤቶች 95 ከመቶ የሚሆነው ለኮሚሽኑ መላኩ ተገልጿል።

XS
SM
MD
LG