በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በክሪሚያ የሚገኝ የሩሲያ የአየር ኃይል ጦር ሰፈር ፍንዳታዎች ደረሱ 


ክሬሚያ በሚገኘው የሩሲያ የአየር ኃይል የጦር ሰፈር የፍንዳታ ድምፅ ከተሰማ በኃላ አካባቢው በጭስ ታፍኖ ታይቷል 
ክሬሚያ በሚገኘው የሩሲያ የአየር ኃይል የጦር ሰፈር የፍንዳታ ድምፅ ከተሰማ በኃላ አካባቢው በጭስ ታፍኖ ታይቷል 

ሩሲያ፣ ህገወጥ በሆነ መንገድ ወደራሷ ግዛት በቀላቀለቻት ክሪሚያ ውስጥ በሚገኘው የሩሲያ የአየር ኃይል የጦር ሰፈር ትናንት በደረሰ ከፍተኛ ፍንዳታ፣ አንድ ሰው ሲሞት አምስት መቁሰላቸው ተነገረ፡፡

ባለሥልጣናት የፍንዳታው መንስኤ ምን እንደሆነ አልገለጹም፡፡

የዓይን እማኞች ትናንት ማከሰኞ በአገሪቱ አቆጣጠር ከቀኑ 9፡15 በኋላ፣ ቢያንስ 12 የሚደርሱ ፍንዳታዎች መድረሳቸውን እንደተመለከቱ ተናግረዋል፡፡

የሩሲያ መካላከያ ሚኒስቴር እ.ኤ.አ. ከ2014 ጀምሮ ሩሲያ በተቆጣጠረችው ሳኪ የጦር ስፈር የነበሩ “በርካታ የአየር ኃይሉ የጥይት ማከማቻ መጋዘኖች” መፈንዳታቸውን አስታውቋል፡፡

ይሁን እንጂ መግለጫው በጦር ሠፈሩም ሆነ በአውሮፕላኖቹ ላይ ጥቃት አለመድረሱን አጽንኦት በመስጠት አስረድቷል፡፡

ጥቃቱን ተከትሎ በዩክሬናውያን የማህበራዊ መገናኛ መድረኮች፣ የኪየቭ ኃይሎች የጦር ሰፈሩን በረጅም ርቀት ሚሳዬሎች መተውታውል የሚል ወሬ በስፋት መሰራጨቱ ተሰምቷል፡፡

ዩክሬን በበኩሏ ጥቃቱን አለማድረሷን አስታውቃለች፡፡

XS
SM
MD
LG