በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በቡርኪናፋሶ  በደረሱ ሁለት ፍንዳታዎች 15 ወታደሮች ተገደሉ 


በቡርኪናፋሶ ማዕከላዊ ሰሜን ግዛት ከቡርዝንጋ ወደ ጂቦ የሚወስደው መንገድ
በቡርኪናፋሶ ማዕከላዊ ሰሜን ግዛት ከቡርዝንጋ ወደ ጂቦ የሚወስደው መንገድ

ቡርኪናፋሶ ውስጥ ትናንት ማክሰኞ በአንድ ጊዜ በደረሱ ሁለት የቦምብ ፍንዳታዎች 15 ወታደሮች መገደላቸው ተነገረ፡፡

ፍንዳታዎቹ የደረሱት የጅሃድ አማጽያንን እየተዋጋች በምትገኘው ቡርኪናፋሶ ማዕከላዊ ሰሜን ግዛት ውስጥ ከቡርዛንጋ ወደ ጂቦ በሚወስደው መንገድ ላይ በተቀበሩ ፈንጂዎች መሆኑን ያገሪቱ ጦር አዛዥ ያወጡት መግለጫ አመልክቷል፡፡

ቡርኪናፋሶ ውስጥ ከአልቃይዳና እስላማዊ መንግስት ጋር ግንኙነት ያላቸው ጅሃዲስቶች እስከዛሬ አድርሰውታል በተባለ ጥቃት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሲገደሉ 1.9 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ ከቤታቸው መፈናቀላቸው ተጠቅሷል፡፡

ባላፈው ጥር ወታደራዊ መንግሥት በመፈንቀለ መንግሥት ሥልጣን በተረከበባት ቡርኪናፋሶ፣ 40 ከመቶ የሚሆነው የአገሪቱ ክፍል ከመንግስት ቁጥጥር ውጭ መሆኑን ተነግሯል፡፡

XS
SM
MD
LG