የአል-ሻባብ ተዋጊዎች ድንበር አቋርጠው እንዳይገቡ ለመከላከል ኢትዮጵያ በመቶ የሚቆጠሩ ወታደሮቿን ሶማሊያ ውስጥ ጌዶ የተባለ አካባቢ ማስፈሯን በደቡብ ምዕራብ ሶማሊያ ያሉ ባለስልጣናት አስታውቀዋል።
የጌዶ አስተዳደር ቃላ አቀባይ አሊ ዩሱፍ አብዱላሂ የኢትዮጵያ ወታደሮች ካለፈው ሳምንት መጨረሻ ጀምሮ ዶሎው በተባለች የድንበር ከተማ ላይ ሲሰባሰቡ መቆየታቸውን እና ካምፕ መመስረታቸውን ለቪኦኤ ተናግረዋል።
/ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/