የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አንተኒ ብሊንከን በአፍሪካ ለሚያደርጉት ጉዞ ደቡብ አፍሪካ ገብተዋል። በቆይታቸውም በደቡብ አፍሪካ የፀረ-አፓርታይድ ትግል ወቅት የነበሩ ቁልፍ ክንዋኔዎችን የሚያወሳውን ሙዚየም የጎበኙ ሲሆን ስሜት ቀስቃሽ ጉዞ መሆኑ ተገልጿል።
ሙዚየሙ እአአ በ1976 በስዌቶ በተካሄደ ዐመፅ ወቅት በፖሊስ እጅ በተገደለው የ12 አመት ታዳጊ ሄክተር ፒተርሰን የተሰየመ ሲሆን፣ ፒተርሰን በወቅቱ የጨቋኞች ቋንቋ ተደርጎ ይታሰብ የነበረው
'አፍሪካንስ' ቋንቋ በትምህርት ቤትውስጥ ጥቅም ላይ መዋሉን ከተቃወሙ ጥቁር ተማሪዎች ውስጥ አንዱ ነበር።
ብሊንከን ከጉብኝታቸው በኃላ ለጋዜጠኞች ባደረጉት ንግግር በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ለዘር እኩልነት የሚደረገውን ትግል አነፃፅረው ጠቅሰዋል።
አያይዘውም "የሄክቶር ታሪክ ጎልቶ የሚሰማን ነው ምክንያቱም እኛም ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የራሳችን የነፃነት እና እኩልነት ትግል አለን። የደቡብ አፍሪካ ታሪክ ልዩ ነው ነገር ግን ደግሞ በጥልቅ ጎልቶ እንዲሰማ የሚያደርግ በርካታ ተመሳሳይ ነገሮችም አሉን።" ብለዋል
/ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/