በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በቤኒሻንጉል በፀጥታ ችግር ምክኒያት ከ79 ቢሊዮን ብር በላይ ሃብት መውደሙ ተገለፀ


አቶ ታረቀኝ ታሲሳ
አቶ ታረቀኝ ታሲሳ

ባለፉት ሁለት ዓመታት ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ በነበረው የጸጥታ ችግር የደረሰውን የጉዳት መጠን እና ለመልሶ ማቋቋም ሥራ የሚያስፈልገውን የገንዘብ አቅም የሚለይ የጥናት ረቂቅ ይፋ መደረጉን የክልሉ መንግሥት አስታወቀ።

የክልሉ አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ታረቀኝ ታሲሳ እስከ አሁን በተደረገው ጥናት ከ475 ሺ በላይ ዜጎች መፈናቀላቸውና ከእነዚያ ውስጥ ደግም ከ200 በላይ የሚሆኑት ወደ አካባቢያቸው መመለሳቸውን አስታውቀዋል።

በጥናቱ በሦስት ዞኖች ውስጥ ከ42ሺ በላይ የግለሰብ ቤቶች፣ ከ200 በላይ የትምህርት ቤቶች፣ ከ189 በላይ የጤና ተቋማትና ሌሎችም መሰረተ ልማቶች በአጠቃላይ በገንዘብ ከ79 ቢሊዮን ብር በላይ በሚያወጣ ሀብት ላይ ጉዳት መድረሱን አቶ ታረቀኝ ተናግረዋል።

ቀሪ ተፈናቃዮችን ለመመለስና መልሶ ለማቋቋም እንዲሁም የወደ መሰረተ ልማቶችን መልሶ ለመገንባት በትብብር ለመሥራት መታቀዱንም ኃላፊው ጨምረው ገልፀዋል።

/ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/

በቤኒሻንጉል በፀጥታ ችግር ምክኒያት ከ79 ቢሊዮን ብር በላይ ሃብት መውደሙ ተገለፀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:37 0:00

XS
SM
MD
LG