በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አሜሪካ ቻይና በታይዋን ዙሪያ የምታደርገው ወታደራዊ ልምምድ አደገኛ ነው አለች


የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አንተኒ ብሊንከን ከደቡብ ኪሪያ አቻቸው ጋ በካምቦዲያ ተገናኝተው በተነጋገሩበት ወቅት - Aug. 5, 2022.
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አንተኒ ብሊንከን ከደቡብ ኪሪያ አቻቸው ጋ በካምቦዲያ ተገናኝተው በተነጋገሩበት ወቅት - Aug. 5, 2022.

የዩናይትድ ስቴስ ምክር ቤት አፈጉባኤ ናንሲ ፐሎሲ በታይዋን ጉብኝት ማድረጋቸው እጅግ ያበሳጫት ቻይና ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር በወታደራዊ ግንኙነት፣ የአየር ንብረት ለውጥ እና በሌሎች ጉዳዮች የምታደርገውን ውይይት ማቋረጧን አስታውቃለች።

የቻይና ጠቅላይ ሚኒስቴር ዋንግ ዪ ጉዳዩን አስመልክቶ ባደረጉት ንግግር "የአሜሪካ ምክርቤት አፈጉባኤ፣ ቻይና በተደጋጋሚ ያሰማችውን ተቃውሞ እና ተደጋጋሚ ድርድር ችላ ብለዋል። ጉዞዋ የተመቻቸውም በዩናይትድ ስቴትስ መንግስት ነው" ብለዋል።

የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ የምስሉን ትክክለኛነት ማጣራት ባይችልም፣ የቻይና ቴሌቭዥን ጣቢያ ቤይጂንግ በታይዋን አቅራቢያ ወታደራዊ ልምምድ ስታደርግና ስትተኩስ የሚያሳዩ ምስሎችን አሳይቷል። ከዚህ በፊት ባልታየ መጠን የሚካሄደው ይህ ልምምድም ዓለም አቀፍ ፍርሃት እና ውግዘት እያስከተለ ነው።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አንተኒ ብሊንከን በካምቦዲያ ጉዞ ባደረጉበት ወቅት ከአሜሪካ ድምፅ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ "የቻይና ምላሽ ያልተመጣጠነ እና አደገኛ ነው" ያሉ ሲሆን ጉዞው ምንም አይነት ስሜት ቢፈጥርባት 11 ተወንጫፊ ሚሳይሎችን በታይዋን ዙሪያ መተኮስ፣ መርከቦችን በታይዋን ዙሪያ ማሰማራት ትክክል አለመሆኑንና ከሚሳይሎቹ አምስቱ ጃፓን አቅራቢያ መውደቃቸውን ገልፀዋል።

XS
SM
MD
LG