በአዲስ አበባ ከተማ እየጣለ ያለው ከባድ ዝናብ የሚያስከትለው ጎርፍ እንደወትሮው ሁሉ በሕይወትና በንብረት ላይ ጉዳት እያደረሰ ነው።
ባለፈው እሁድ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አማኑኤል ሆስፒታል አካባቢ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ የሌሎችን ሕይወት ለማዳን ሲጥር የነበረ አንድ ታዳጊ ወጣት ሕይወት አልፏል፡፡
የሟቹን ቤተሰቦች ጨምሮ ንብረታቸውን በሙሉ ያጡ የአደጋው ተጎጂዎች ለችግር መጋለጣቸውን ገልፀዋል።
በክረምቱ የጎርፍ አደጋ የሁለት ሰዎች ሕይወት ማለፉን ለቪኦኤ የገለጸው የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ለተጎጂዎች ስለሚደረገው ድጋፍ ለተነሳለት ጥያቄም ምላሽ ሰጥቷል፡፡
/ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/