በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የደቡብ ሱዳን የሽግግር መንግሥት ዘመን ተራዘመ


ፎቶ ፋይል፦ የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር
ፎቶ ፋይል፦ የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር

የደቡብ ሱዳን መሪዎች የሽግግር መንግሥቱን ለተጨማሪ ሁለት ዓመት አራዝመዋል።

ህጋዊነቱ ላይ ጥያቄ ቢነሳባቸውም የሃገሪቱ ይሽግግር መንግሥት ለተጨማሪ 24 ወራት እንዲቀጥል የደቡብ ሱዳን ባለሥልጣናት ወስነዋል።

ዘመኑን ማራዘም ያስፈለገው ‘የፖለቲካ፤ የደኅንንነትና የምርጫ ማሻሻያ ሥራዎችን ለማጠናቀቅ ነው’ ተብሏል።

የሽግግሩን መንግሥት ጊዜ የማራዘሙ ውሳኔ የደቡብ ሱዳንን የርስ በርስ ጦርነት ያስቆመውን የ2011 ዓ.ም. የሰላም ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ እንቅፋት የሆኑትን ጉዳዮች ለመፍታት እንደሚረዳ የካቢኔ ጉዳዮች ምኒስትሩ ኢሊያ ሎሙሮ ገልፀዋል።

ደቡብ ሱዳን ውስጥ ለአራት ዓመት ተኩል የተካሄደው የእርስ በርስ ጦርነት የ400 መቶ ሺህ ሰው ህይወት ቀጥፏል።

ውሳኔው በየካቲት 2012 ዓ.ም. የተጀመረውን የሽግግር መንግሥቱን ዘመን ‘ፍፃሜ አልሰጡትም’ በሚሏቸው የደቡብ ሱዳን መሪዎች ሥራ ያልተደሰተውን ዓለምአቀፍ ማኅበረሰብ ሊያስቆጣ ይችላል ተብሏል።

“የሰላም ስምምነቱን ሙሉ በሙሉ ለመፈፀም መሪዎቹ አዝግመዋል” ሲሉ ባለሙያዎች ትችት እያሰሙ ነው።

ከዚህ በተጨማሪም የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር እና ምክትላቸው ሪክ ማቻር ‘ቋሚ ህገ መንግሥት የለንም’ በሚል ምርጫውን በሁለት ዓመት አዛውረውታል።

በአንዳንድ የሃገሪቱ ክፍሎች አሁንም መረጋጋት ስሌለ ነፃ፣ ፍትኃዊና ሰላማዊ ምርጫ ለማካሄድ አይቻልም የሚሉ ደቡብ ሱዳን የሚገኙ የሲቪል ማኅበረሰብ ቡድኖች በውሳኔው እንደሚስማሙ አስታውቀዋል።

የመንግሥት ሠራዊት በሆነው የመከላከያ ኃይልና በአማፂው ‘በሱዳን ህዝብ ነፃነት ንቅናቄ - በተቃውሞ’ መካከል ያለው የትጥቅ ፍጥጫ አንድ ብሄራዊ መከላከያ ለመፍጠር በሚደረገው ጥረት ላይ እንቅፋት ሆኗል።

‘ሁለቱም ወገኖች የፖለቲካና የደኅንነት ቀውሱን ለማስቆም አስፈላጊውን ማሻሻያ አላመጡም’ በሚል ዩናይትድ ስቴትስ ከሰላም ሂደቱ መውጣቷን ባለፈው ወር አስታውቃለች።

XS
SM
MD
LG