በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዝንጀሮ ፈንጣጣ “አጣዳፊ የማኅበረስብ ጤና ችግር” ነው


የዝንጀሮ ፈንጣጣ ወረርሽኝ
የዝንጀሮ ፈንጣጣ ወረርሽኝ

ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በፍጥነት እየተዛመተ ያለውን መንኪ ፖክስ ወይም የዝንጀሮ ፈንጣጣ ወረርሽኝ “አጣዳፊ የማኅበረስብ ጤና ችግር” ነው ሲል መንግሥቱ ትናንት አስታውቋል።

መግለጫው ክትባትና መድኃኒት ባፋጣኝ ለማዳረስ እንዲቻል ቢሮክራሲያዊ ማነቆዎችን ይቀንሳል ተብሏል።

የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሃገሪቱ “አጣዳፊ የማኅበረስብ ጤና ችግር” መሆኑን የጤና ሚኒስትሩ ሃቪየር ባሴራ ናቸው።

“በቫይረሱ ላይ የምናደርገውን ዘመቻ ወደሚቀጥለው ደረጃ ለማሳደግ ዝግጁ ነን፤ ተውሳኩን ለማጥፋት ሁሉም አሜሪካዊ ትኩረት እንዲሰጠው እናበረታታለን” ብለዋል የጤና ምኒስትሩ።

መንግሥት ‘በተለይም ክትባትን በተመለከተ የወሰደው እርምጃ በጣም አዝጋሚ ነበር’ ስለሚለው ነቀፌታ የተጠየቁት የዋይት ሃውስ ፕሬስ ኃላፊ ካሪን ዣን-ፒየር በሽታው ግንቦት ውስጥ ሲከሰት እንደ ትልቅ ችግር አለመታየቱን አስታውሰዋል።

አሁን ሁኔታው መቀየሩንና በቫይረሱ ተፈጥሮ ምክንያትም በፍጥነት እየተዛመተ መሆኑን የፕሬስ ኃላፊዋ ጠቁመዋል።

እስከ አሁን ከሰባት ሺህ በላይ ሰው ለቫይረሱ የተጋለጠ መሆኑና ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በአብዛኛው ከተመሳሳይ ፆታ ጋር ግንኙነት በሚያደርጉ ወንዶች ላይ እንደሚታይ ተገልጿል።

XS
SM
MD
LG