ደቡብ ክልል ውስጥ የሚገኙና በአቀማመጥ ይቀራረባሉ የተባሉ ዞኖች እና ወረዳዎች ተጣምረው ሁለት የተለያዩ ክልሎችን እንዲመሰርቱ በየምክር ቤታቸው ያሳለፉት የውሳኔ ሐሳብ ድጋፍ እና ተቃውሞ ገጥሞታል።
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የልማት ጥናት ትምሕርት ክፍል ተባባሪ ፕሮፌሰር ዶክተር ፊልሞን ሀዳሮ ፤ ውሳኔው በክልሉ ነዋሪዎች የተነሱ ጥያቄዎችን ይፈታል ብለው አያምኑም። ክልሉ አንድ ሆኖ ቢቀጥል የተሻለ ነው የሚል አቋም አላቸው።
በሐዋሳ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስ መምሕር ዶክተር ንጉስ ደግሞ ውሳኔው ተገቢነት ያለውና ኢትዮጵያ ያለችበትን ወቅታዊ ሁኔታ ከግንዛቤ ውስጥ ያስገባ ነው ብለዋል።
/ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/