በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እርዳታ የራቃቸው የኮንሶ ዞን የድርቅ ተጠቂዎች


እርዳታ የራቃቸው የኮንሶ ዞን የድርቅ ተጠቂዎች
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:46 0:00

እርዳታ የራቃቸው የኮንሶ ዞን የድርቅ ተጠቂዎች

በኮንሶ ዞን በድርቅ የተጎዱ ዜጎች፣ በቂ ድጋፍ እንዳልቀረበላቸው በስልክ ለአሜሪካ ድምፅ ገለጹ።

ችግሩ፣ ለአንድ ወር እንኳን በዚኹ ከቀጠለ የሚያደርሰው ጉዳት የከፋ ነው፤ ሲሉም ተጎጂዎቹ ስጋታቸውን ተናግረዋል። ከአሜሪካ ድምፅ ጋራ ቃለ ምልልስ ያደረጉት የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ ዳዊት ገበየሁ፣ በዞኑ ከፍተኛ ድርቅ መኖሩን ጠቅሰው፣ እየቀረበ ያለው ድጋፍ ውስን መኾኑን አረጋግጠዋል።

በዞኑ ከ190ሺሕ በላይ ዜጎች አስቸኳይ የምግብ ርዳታ እንደሚሹ ያስታወቀው የዞኑ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን፣ እየቀረበ ያለው ድጋፍ ግን 30 በመቶ ብቻ እንደኾነ ገልጿል። በዐዲስ አበባ የሚኖሩ እና ከዞኑ ውጭ ያሉ የኮንሶ ወላጆች እና ወዳጆች፣ ብር 800 ሺሕ ያኽል ለድጋፍ መሰብሰባቸውን አስተባባሪ ኮሚቴው አስታውቋል።

በዞኑ በተከሠተ ድርቅ የተነሳ፣ ስምንት ሕፃናት እንደሞቱ፣ የካራት ሆስፒታል ለአሜሪካ ድምፅ ማረጋገጡን መዘገባችን ይታወሳል።

XS
SM
MD
LG