በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የም/ቤት አባላት እና የደቡብ ክልል መንግሥት የተዋቀሱበት የዜጎች ጥቃት እና ተጋላጭነት


የም/ቤት አባላት እና የደቡብ ክልል መንግሥት የተዋቀሱበት የዜጎች ጥቃት እና ተጋላጭነት
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:22 0:00

የም/ቤት አባላት እና የደቡብ ክልል መንግሥት የተዋቀሱበት የዜጎች ጥቃት እና ተጋላጭነት

የደቡብ ክልል ምክር ቤት አባላት፣ “ለዜጎች ደኅንነት ትኩረት አልሰጠም፤” ያሉትን የክልሉን መንግሥት ተቹ። የደቡብ ክልል መንግሥት፣ የታጠቁ ኀይሎች እና የጸጥታ ችግሮች ባሉባቸው አካባቢዎች የሚገኙ ዜጎችን ደኅንነት መጠበቅ እንዳልቻለ የገለጹት የምክር ቤቱ አባላት፣ የክልሉን መንግሥት ወቅሰዋል።

እየተገባደደ በሚገኘው በ2014 ዓ.ም. በኮንሶ ዞን፥ አማሮ፣ ቡርጂ፣ ደራሼ፣ አሌ ልዩ ወረዳዎች እንዲሁም፣ በባስኬቶ እና ሰላማጎ ወረዳዎች ውስጥ የጸጥታ ችግር መከሠቱን የምክር ቤቱ አባላት ገልጸዋል። ሕዝቡ ለሚያቀርባቸው ጥያቄዎች በፍጥነት እና በተገቢው መንገድ ምላሽ አለመስጠት ለችግሩ መባባስ ዋና ምክንያት እንደኾነ አባላቱ አስረድተዋል።

በሌላ በኩል፣ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል በልዩ ልዩ አካባቢዎች በተፈጠሩ የጸጥታ ችግሮች ምክንያት የብዙ ሰዎች ሕይወት መጥፋቱን የገለጹት የክልሉ ፕሬዝዳንት አቶ ርስቱ ይርዳው የገለጹ ሲኾን፣ ለዚኽም ፖለቲካውን ወቅሰዋል።

/ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/

XS
SM
MD
LG