በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አሜሪካ እና ሩሲያ በእስረኛ ልውውጥ ዙሪያ ተወያዩ


የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር አንተኒ ብሊንከን በዩናይትድ ስቴትስ እና ጃፓን የኢኮኖሚ ፖሊሲ ምክክር ኮሚቴ ስብሰባ ላይ ንግግር ሲያደርጉ 
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር አንተኒ ብሊንከን በዩናይትድ ስቴትስ እና ጃፓን የኢኮኖሚ ፖሊሲ ምክክር ኮሚቴ ስብሰባ ላይ ንግግር ሲያደርጉ 

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አንተኒ ብሊንከን ትላንት ከሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሰርጌ ላቭሮቭ ጋር በስልክ ተገናኝተው አሜሪካ በሩሲያ በእስር ላይ የምትገኘውን የቅርጫት ኳስ ተጫዋች ብሪትኒ ግሪነርን እና የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ የባህር ኃይል አባል ፓውል ዌለን እንድትለቅ ያቀረበችውን ሐሳብ እንድትቀበል ጠይቀዋል።

የስልክ ጥሪው ሩሲያ በየካቲት ወር በዩክሬን ላይ ወረራ ከፈፀመች ወዲህ ሁለቱ ከፍተኛ ዲፕሎማቶች ለመጀመሪያ ጊዜ ያደረጉት ንግግር ሲሆን ዩናይትድ ስቴትስ በሁለቱ አማሪካውያኖች ምትክ ህገወጥ መሳሪያ በማዘዋወር የተፈረደበትን ሩሲያዊ ቪክቶር ባውት ወደ ሞስኮ እንደምትልክ አስታውቃለች።

አሜሪካ ያቀረበችውን የእስረኛ ልውውጥ ጥያቄ ተከትሎ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን የገለፀው ነገር ባይኖርም አሜሪካ 'ሰላማዊ ዲፕሎማሲ' አልተከተለችም በሚል ግን ቁጣውን ግለጿል።

XS
SM
MD
LG