በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፌስቡክ በኬንያ የዘር ግጭት የሚያነሳሳ የጥላቻ ንግግር አፅድቋል - ሪፖርት


ፋይል - ምርጫው ሰላማዊ እና ከምርጫ በኃላ በሚነሳ ግጭት ጥቃት ለደረሰባቸው ፍትህ በሚጠይቅ ሰልፍ ላይ ተቃዋሚዎች መፈክር ሲያሰሙ 
ፋይል - ምርጫው ሰላማዊ እና ከምርጫ በኃላ በሚነሳ ግጭት ጥቃት ለደረሰባቸው ፍትህ በሚጠይቅ ሰልፍ ላይ ተቃዋሚዎች መፈክር ሲያሰሙ 

በኬንያ በነሐሴ ወር ከሚካሄደው ምርጫ ጋር ተያይዞ ፌስቡክ የጥላቻ ንግግርን ከገፁ ላይ እንዲያጠፋ የኬንያ ባለስልጣናት ጠይቀዋል። ግሎባል ዊትነስ የተባለ የመብት ቡድን ባወጣው ሪፖርት የማህበራዊ ሚዲያ ኩባንያው የዘር ግጭት የሚቀሰቅሱ የጥላቻ ንግግሮች ያሉባቸው ማስታወቂያዎችን ማፅደቁን ይፋ አድርጓል።

ግሎባል ዊትነስ በጥናቱ ሂደቱ 10 በእንግሊዘኛ እና 10 በስዋሂሊ ቋንቋ የተሰሩ የጥላቻ ንግግር ያዘሉ ማስታወቂያዎችን ለፌስቡክ ያስተላለፈ ሲሆን ሁሉም ማስታወቂያዎች መፅደቃቸውን የተቋሙ ዋና አማካሪ ጆን ሎይድ ተናግረዋል።

በኬንያ ፌስቡክ ከ10 ሚሊየን በላይ ተጠቃሚዎች ያሉት ሲሆን በነሐሴ ወር የሚካሄደውን ምርጫ ተከትሎ በማህበራዊ ድህረገፁ የዘር ግጭትን የማስፋፋት እና ሀሰተኛ መረጃዎችን ሆን ብሎ የማሰራጨት አደጋ መኖሩን ባለሙያዎች አስጠንቅቀዋል።

ሪፖርቱን ተከትሎ ፌስቡክ ትላንት ባወጣው መግለጫ የተወሰኑ የጥላቻ ንግግሮች በገፁ መተላለፉን አምኖ ችግሩ የተፈጠረው ድህረገፁ የሚጠቀማቸው ማሽኖች እና ሰዎች በሰሩት ስህተት ነው ብሏል። አክሎም፣ በተለይ የስዋሂሊ ቋንቋ ተናጋሪዎች እና ቴክኖሎጂዎች ጎጂ መረጃዎችን በማስወገድ እንዲያግዙት እና ምርጫው ሰላማዊ እና ስጋት የሌለበት እንዲሆን በሰዎች ላይ እና ቴክኖሎጂዎች ላይ እንዲሰራ ጠይቋል።

XS
SM
MD
LG