በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኦሬገን የገቡ የኤርትራ አትሌቶች ተሰወሩ


ፎቶ ፋይል፦ እንደጠፉ ከተገለጹት መካከል አንዱ ኤርትራዊው አትሌት የማነ ተኽለሃዪም
ፎቶ ፋይል፦ እንደጠፉ ከተገለጹት መካከል አንዱ ኤርትራዊው አትሌት የማነ ተኽለሃዪም

ዩናይትድ ስቴትስ፤ ዩጂን-ኦሬገን በተካሄደው 18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ለመሳተፍ የተላኩ አራት የኤርትራ አትሌትና አንድ አሠልጣኛቸው የገቡበት መጥፋቱን የኦሬገን ስቴት ፖሊስን ጠቅሶ ኬቪኤኤል ኒውስ የሚባል የአካባቢው ቴሌቪዥን ጣቢያ ዘገበ።

አትሌቶቹ በጊዜያዊነት አርፈውበት በነበረው የአንድ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ለመጨረሻ ጊዜ የታዩት ባለፈው ቅዳሜ፤ ሐምሌ 16/2014 ዓ.ም. እንደነበረ ዘገባው ጠቁሟል።

አትሌቶቹና አሠልጣኛቸው ያሉበትን የሚያውቅ 541-346-2919 ላይ ደውሎ መረጃ እንዲሰጥ ጥያቄ ያቀረበው የኦሬገን ስቴት ፖሊስ “የት እንደገቡ ማወቅ አልቻልኩም” ያላቸውና ስሞቻቸውን ከነዕድሜአቸው ያወጣቸው አንዴ ፊልሞን (24 ዓመት)፣ ሃብቶም ሳሙዔል (18 ዓመት)፣ በርኸ አስገዶም (44 ዓመት)፣ መሃሪ መብራህቱ (18 ዓመት)ና የማነ ተኽለሃዪም (24 ዓመት) መሆናቸውን አስታውቋል።

በአትሌቶቹ ላይ የተፈፀመ የኃይል አድራጎት ስለመኖሩ መረጃ እንደሌለው የጠቀሰው የስቴቱ ፖሊስ ለፌዴራልና ለአካባቢው ህግ አስከባሪና አጋር ኤጀንሲዎች ማሳወቁን መግለፁን ኬቪኤኤል አክሎ ዘግቧል።

ተጨማሪና ዝርዝር መረጃ ለማግኘት እየጣርን ነን።

XS
SM
MD
LG