በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለድርድሩ ቅድመ ሁኔታ እና ጊዜ ገደብ ማስቀመጣቸውን ዶ/ር ደብረጽዮን ተናገሩ


ለድርድሩ ቅድመ ሁኔታ እና ጊዜ ገደብ ማስቀመጣቸውን ዶ/ር ደብረጽዮን ተናገሩ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:16 0:00

ለድርድሩ ቅድመ ሁኔታ እና ጊዜ ገደብ ማስቀመጣቸውን ዶ/ር ደብረጽዮን ተናገሩ

በትግራይ ክልል እና በኢትዮጵያ መንግሥት በኩል ይደረጋል ለተባለው ድርድር ወይም ውይይት ቅድም ሁኔታ እና የጊዜ ገደብ መቀመጡን ትግራይ ክልልን በመምራት ላይ ሚገኙት እና የህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረ ሚካኤል ተናገሩ። ጦርነቱ በሰላማዊ እና ፖለቲካዊ ውይይት እንዲጠናቀቅ ፍላጎታቸው መሆኑንንም ተናግረዋል።

በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ለክልሉ ቴሌቭዥን ጣቢያ መግለጫ የሰጡት ዶ/ር ደብረጽዮን ይደረጋል የተባለውን ውይይት በዋነኛነት የሚመሩት አሜሪካኖች መሆናቸውን ጠቅሰው፤ “የሰላም ውይይቱን ለመጀመር አስቀድሞ መሰረታዊ አገልግሎቶች ተመልሰው መከፈት አለባቸው” ብለዋል።

“ሕገ መንግሥትን መሰረት ያደረገ ድርድር ለማካሄድ ዝግጁ ነን” ያሉት ዶ/ር ደብረጽዮን ውይይቱን እየተከታተሉ ነው ላሏቸው አሜሪካኖች፤ “አገልግሎት የሚጀመርበትን ጊዜ ቁርጡን ንገሩን። ቃላቸውን የሚጠብቁ ካልሆነም ንገሩን። ያስቸገራቸው ነገር ካለም ንገሩን ብለን ለመጨረሻ ግዜ የጊዜ ገደብ ሰጥተናቸዋል። የማይመልሱ ከሆነም ለኛ መልስ ነው። አልፈለጉም ማለት ነው። የሚመልሱ ከሆነ ደግሞ ስለ አፈፃፀሙ እናወራለን። ዝም ብለን መጠበቅ የሚባል ነገር የለም።” ብለዋል።

ተሰጠ ያሉት የጊዜ ገደብ ለምን ያህል ጊዜ እንደሆና ባይናገሩም፤ ካልሆነ ግን ወደ ውጊያ እንደሚገቡ ገልፀው ማስጠንቀቃቸውን ተናግረዋል።

በዚህ የህወሓት መሪ አስተያየት ላይ ከዩናይትድ ስቴትስ በኩል የተሰማ ቀጥተኛ ምላሽ የለም።

ይሄም ሆኖ በኢትዮጵያ መንግሥትእና በህወሓት መካከል ሊካሄድ የታሰበው የሠላም ውይይት በአፍሪካ ሕብረት አመቻችነት መካሄዱን አገራቸው እንደምትደግፍ በአዲስ አበባ የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ጉዳይ ፈጻሚ አምባሳደር ትሬሲ ጃኮብሰን ተናግረዋል።

ዝርዝር ጉዳዮች ግን ለሁለቱ ተደራዳሪ ወገኖች የሚተው መሆናቸውን ጠቁመዋል ።

“ዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ሕብረትንሙሉ በሙሉ ትደግፋለች።በዚህ ኤምባሲ ቅጥር ግቢም የአፍሪካ ሕብረት ኤምባሲና ቋሚ ተወካይአለን።” ያሉት አምባሳደር ትሬሲ ጃኮብሰን “የሠላም ውይይቱ እንዴት ይካሄድ፣ የት እና የመሳሰሉት ዝርዝሮች ለተደራዳሪዎቹ ለራሳቸው የሚተው ናቸው። ያ እንዴት መሆን እንዳለበት እና ማን ምን ማድረግ እንዳለበት አቋም እየያዝን አይደለም። ውይይቱ መካሄዱ አስፈላጊ ነው። በቶሎ መጀመርም አለባቸው። የትኛዎቹም ባለድርሻ አካላት በየትኛውም በሚጠይቁን መንገድ ልናግዛቸው ዝግጁ እንሆናለን።” ብለዋል።

/ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/

XS
SM
MD
LG