በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ ለኢትዮጵያ ተጨማሪ ድጋፍ አደረገች


ዩናይትድ ስቴትስ ለኢትዮጵያ ተጨማሪ ድጋፍ አደረገች
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:16 0:00

ዩናይትድ ስቴትስ ለኢትዮጵያ ተጨማሪ ድጋፍ አደረገች

ለአስከፊው የኢትዮጵያ ድርቅ ምላሽ የሚሆን 488 ሚሊዮን ዶላር ተጨማሪ ሰብዓዊ ድጋፍ ማድረጓን ዩናይትድ ስቴትስ ዛሬ አስታውቃለች።

አሁን የሚታየው ድርቅ በታሪክ እጅግ የከፋው መሆኑን የገለፁት በኢትዮጵያ ዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ጉዳይ ፈጻሚ አምባሳደር ትሬሲ ጃኮብሰን አገራቸዉ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኗን ተናግረዋል ።

ወደ ትግራይ የተላከውን የምግብ ዕርዳታ ለማሰራጨት እና ለማከፋፈል የሚረዳ ነዳጅ የጫኑ የመጀመሪያዎቹ ተሽከርካሪዎች ከጅቡቲ ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸውንም አምባሳደር ጃኮብሰን ዛሬ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

እንደ ዩናይትድ ስቴትስ ዓይነት ሰብዓዊ አጋሮች በወር አስከ ሁለት ሚሊዮን ሊትር ነዳጅ ከቀረጥ ነጻ እንዲያስገቡ የኢትዮጵያ መንግሥት መፍቀዱንም ጠቁመዋል።

/ሙሉውን የተያያዘው ፋይል ያዳምጡ/

XS
SM
MD
LG