በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“ድንበር አቋርጠው ኢትዮጵያ የገቡት የአልሻባብ ታጥቂዎች ኢትዮጵያውያን ናቸው” - አቶ ሙስጠፌ ሙሐምድ


“ድንበር አቋርጠው ኢትዮጵያ የገቡት የአልሻባብ ታጥቂዎች ኢትዮጵያውያን ናቸው” - አቶ ሙስጠፌ ሙሐምድ
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:21 0:00

“ድንበር አቋርጠው ኢትዮጵያ የገቡት የአልሻባብ ታጥቂዎች ኢትዮጵያውያን ናቸው” - አቶ ሙስጠፌ ሙሐምድ

የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ሐምሌ 13 ቀን ኢትዮጵያን ድምበር አቋርጦ ከገባው የአልሻባብ ታጣጊቂዎች ጋር በተደረገው ውጊያ 100 ተዋጊዎች መገደላቸውን እና 13 መኪናዎቻቸው መውደማቸውን ያስታወቀ ሲሆን የክልሉ ፕሬዚዳንት ሙስጠፌ መሐመድ የኢትዮጵያን ድንበር አቋርጠው የገቡት የአልሻባባ ታጣቂዎች ቅርንጫፍ ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን ተናገሩ።

የሶማሌ ባለሥልጣናት እና በጉዳዩ ላይ እውቀት ያላቸው ባለሞያዎች የአልሻባብ ተዋጊዎች ኢትዮጵያ ውስጥ መግባታቸውን እና አሁንም ድረስ እንቅስቃሴ ላይ መሆናቸውን ይገልፃሉ።

ኦማር መሐመድ አቡ አያን የተባሉ አሁን ኑሯቸውን በስዊድን ያደረጉ የቀድሞ የአልሻባብ ባለሥልጣን እንዲሁም ለደህነታቸው ሲሉ ስማቸው እንዳይገለፅ የጠየቁ ሌላ የአል ሻባብ የቀድሞ ኃላፊ ለቪኦኤ የሶማሊኛ ቋንቋ አገልግሎት እንደገለፁት አልሻባብ ኢትዮጵያ ውስጥ እያደረገ የሚገኘውን እንቅስቃሴ የሚመሩት ትውልዳቸው ከኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የሆነ አሊ ዲያር የተባሉ አንጋፋ የአል-ሻባብ ኮማንደር ናቸው።

የአልሻባብ ተዋጊዎች ዕሮብ እለት በሶማሌ ክልል በሚገኙት የድ፣ አቶ እና ዋሻቆ የተባሉ ከተሞች ድንገተኛ ጥቃት ከማድረሳቸው በፊት በደቡብ ምዕራብ የሚገኘውን የስልክ አገልግሎት ሙሉ ለሙሉ እንዲቋረጥ አድርገው ነበር። የቀድሞ የአል ሻባብ ባልደረቦች ለአሜሪካ ድምፅ ሶማሌ አገልግሎት እንደገለፁት ወደ ኢትዮጵያ ከገቡት 500 የአልሸባብ ተዋጊዎች ውስጥ ከሶማሌ እና ኦሮሚያ ክልል የተቀላቀሉ ተዋጊዎች ይገኙበታል።

ቡድኑ የመጀመሪያውን ጥቃት ያደረሰበት በሶማሌ ክልል የሚገኘው ባኮል ከተማ አስተዳዳሪ የሆኑት መሀመድ አብዲ ታል እንዳረጋገጡትም፣ በወረራው የተሳተፉት አብዛኞቹ የአል-ሻባብ ተዋጊዎች ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ በሶማሊያ ጁባ ክልል የሰለጠኑ እና ከአልሻባብ ጋር ኀብረት ያላቸው ናቸው። ሁለት ቡድኖች መኖራቸውን እና አንዱ በድንበር ላይ የሚዋጋ ሲሆን ሌላው አልፎ መግባቱንም ገልፀዋል።

ስማቸውን መግለፅ ያልፈለጉት የቀድሞ የአል-ሻባብ አባል እንደሚሉት የቡድኑ አላማ ኢትዮጵያ ውስጥ ጥቁር ባንዲራቸውን መስቀል እና ጂሃድ በአፍሪካ ቀንድ አዲስ ግንባር መስፋፋት መጀመሩን የሚገልፅ መግለጫ ማወጅ መሆኑን ገልፀዋል። በኬንያ እና በሶማሊያ ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያ ውስጥም መንቀሳቀስ የሚችሉ መሆናቸውን ማሳየት እንደሚፈልጉም የቀድሞ የአልሻባብ ኃላፊ አቡ አያል አብራርተዋል።

የአፍሪካ ቀንድ ጉዳዮች ተንታኝ የሆኑት ማት ብራይደን ይህ አልሻባብ ያደረሰው ጥቃት ምናልባት ወደፊት በኢትዮጵያ በቋሚነት የሚንቀሳቀስ ተዋጊ እንዲኖር ለማድረግ የታሰበ ስልታዊ ዓላማ መጀመሪያ ሊሆን ይችላል ይላሉ። ይህ ተዋጊ ቡድን በሶማሊያ እና በኦሮሚያ ክልሎች መሃከል በሚገኘው የባሌ ተራራዎች ላይ ሊሰፍር እንደሚችልም ይጠቅሳሉ።

ብራይደን አክለው፣ ቡድኑ ምናልባት አሁን ሽንፈት ቢደርስበት እንኳን አልሻባብ ኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ ወታደራዊ እንቅስቃሴ የማድረግ አቅም እንዳለው የማሳየት አላማቸውን አሳክተዋል ብለዋል።

የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ምስጠፌ ሙሐምድ፤ ቡድኑ ኢትዮጵያ ውስሽ ሽብር ፈፅሞ ለመሄድ የተለያዩ እንቅስቃሴዎቹ ሲያደርግ መቆየቱን ገልፀ አሁን ግን የኢትዮጵያን ድንበር ሰባት ኪሎ ሜትር አልፎ የገባው ቡድን በሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል መደምሰሱን ተናግረዋል።

/ከሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት ሙስጠፌ ሙሐመድ ጋራ የተደረገውን ቃለ ምልልስ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/

XS
SM
MD
LG