በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በአፍሪካ ለሚያደርጉት ጉብኝት ግብፅ ገቡ


የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሰርጌይ ላቭሮቭ ከግብፅ አቻቸው ሳሜህ ሹክሪ ጋር በካይሮ ሲገናኙ 
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሰርጌይ ላቭሮቭ ከግብፅ አቻቸው ሳሜህ ሹክሪ ጋር በካይሮ ሲገናኙ 

በዩክሬን ላይ በፈፀመችው ወረራ ምክንያት ከምዕራብ ሀገራት ከተጣለባት ማዕቀቦች እና ዲፕሎማሲያዊ መገለል ለመውጣት ጥረት እያደረገች የምትገኘው ሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሰርጌይ ላቭሮቭ ትላንት ማታ ካይሮ ገብተዋል።

የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ጠዋት ከግብፅ አቻቸው ሳሜህ ሹክሪ ጋር ተገናኝተው የተነጋገሩ ሲሆን፣ ከአረብ ሊግ ዋና ፀሃፊ አህመድ አቡል ጋይት እና ከፓን አረብ ድርጅት ቋሚ ተወካዮች ጋርም ለመገናኘት ቀጠሮ ተይዞላቸዋል።

ላቭሮቭ በአፍሪካ ለሚያደርጉት ጉብኝት ግብፅ የመጀመሪያ ማረፊያቸው ትሁን እንጂ በቀጣይ ወደ ኢትዮጵያ፣ ዩጋንዳ እና ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የሚያቀኑ ይሆናል።

በሩሲያ እና በዩክሬን መሀከል የሚደረገው ጦርነት ከሩሲያ ይላኩ የነበሩ ምርቶችን የማጓጓዝ ስራን ያደናቀፈ ሲሆን በርካታ የአፍሪካ ሀገሮች ጦርነቱ ተፅእኖ ካደረሰባቸው ሀገሮች መሀከል ናቸው። በዚህ ምክንያት እጅግ ተፈላጊ የሆኑ ሸቀጦች ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ የጨመረ ሲሆን በእርዳታ መልክ ይደርስ የነበረው በቢሊየን የሚቆጠር ዶላርም በጦርነቱ ምክንያት አውሮፓ ውስጥ ለተፈናቀሉ ሰዎች እንዲደርስ በመደረጉ በአፍሪካ እና በመካከለኛው ምስራቅ የሚኖሩ በርካታ ሰዎች በከፍተኛ ምግብ እጥረት እንዲሰቃዩ አድርጓል።

XS
SM
MD
LG