ኢትዮጵያ በ2014 ዓ.ም የበጀት ዓመት ከአራት ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ማግኘቷ ተገለፀ፡፡ ትላንት በአዲስ አበባ በተከበረው የኢትዮጵያ የውጪ ንግድ ቀን ላይ ንግግር ያደረጉት የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር አቶ ገብረመስቀል ጫላ፤ “ከውጪ ንግድ ይህን ያህል ገቢ ሲገኝ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ነው” ብለዋል።
ሆኖም ግን ዘርፉ በተለያዩ ችግሮች ምክኒያት ፈተና ውስጥ መሆኑን ተናግረዋል። በሀገሪቱ ውስጥ ያለው አለመረጋጋት እና የአገዋ የገበያ ዕድል መቋረጥ ከችግሮቹ መካከል የተወሰኑት እንደሆኑ ጠቅሰዋል።
/ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ/