በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቴክሳስ ውስጥ መኪና ውስጥ ሞተው በተገኙት 53 ፍልሰተኞች ጉዳይ 2 ሰዎች ተከሰሱ


ፍልሰተኞችን በህገ ወጥ መንገድ በማጓጓዝ እና ለማጓጓዝ በማሴር እንዲሁም በዚህ አድራጎታቸው ፍልሰተኞቹን ለሞት በመዳረግ ረቡዕ ዕለት ክስ ተመስርቶባቸዋል።  
ፍልሰተኞችን በህገ ወጥ መንገድ በማጓጓዝ እና ለማጓጓዝ በማሴር እንዲሁም በዚህ አድራጎታቸው ፍልሰተኞቹን ለሞት በመዳረግ ረቡዕ ዕለት ክስ ተመስርቶባቸዋል።  

በቅርቡ ዩናይትድ ስቴትስ ቴክሳስ ክፍለ ሀገር ሳን አንቶኒዮ ከተማ ውስጥ በግዙፍ የግብርና ዕቃ ማጓጓዣ መኪና ውስጥ ሀምሳ ሶስት ፍልሰተኞች ህይወታቸው አልፎ ከተገኙበት በተያያዘ ሁለት ሰዎች ላይ ክስ ተመስርቷል።

ዛሞራኖ እና ክሪስቲያን ማርቲኔዝ የተባሉት ሁለቱ የቴክሳስ ፓሳዲና ከተማ ነዋሪዎች ፍልሰተኞችን በህገ ወጥ መንገድ በማጓጓዝ እና ለማጓጓዝ በማሴር እንዲሁም በዚህ አድራጎታቸው ፍልሰተኞቹን ለሞት በመዳረግ ረቡዕ ዕለት ክስ ተመስርቶባቸዋል።

ለሞት በመዳረግ የሚለው የወንጀል ክስ በዕድሜ ልክ እስራት ሊያስቀጣቸው እንደሚችል የተገለጸ ሲሆን የሳን አንቶኒዮ ዐቃብያነ ህግ ፍርድ ቤት የሞት ቅጣት እንዲበይንባቸው ሊጠይቁ እንደሚችሉ ተመልክቷል።

XS
SM
MD
LG