የጣልያን ጠቅላይ ሚኒስትር ማሪ ድራጊ የተከፋፈለ መንግሥታቸውን ወደ አንድነት ለማምጣት ያደረጉት ጥረት ባለመሳካቱ ሥልጣን መልቀቃቸውን ዛሬ አስታውቀዋል።
የፕሬዚዳንት ሴርጂዮ ማታሬላ ፅህፈት ቤት የጠቅላይ ሚኒስትሩን መልቀቂያ መቀበሉን አስታውቋል።
ይሁን እንጂ አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር እስኪተካ ድራጊ በሞግዚትነት እንዲቆዩ ፕሬዚዳንቱ መጠየቃቸው ተገልጿል።
በዚህ ምክንያት ጣልያን ለሚቀጥለው ዓመት የታቀደውን የፓርላማ ምርጭ ጊዜ ሳትጠብቅ በሚቀጥሉት ወራት ውስጥ ምርጫ ልታካሂድ እንደምትችል ተሰምቷል።