በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአሜሪካ የድምፅ ቆጠራ ህግ የወደፊት ዕጣ

ፎቶ ፋይል፦ በምርጫ ድምፅ አቆጣጠር ህግ ላይ ለውጥ እንዲኖር የሚያስችል ስምምነት ላይ መድረሳቸውን የገለጹት የዩናይትድ ስቴትስ ሁለቱ ዋና ዋና ፓርቲዎች እንደራሴዎች ቡድን መሪ የሆኑት የሜይን ዴሞክራት፣ ሴነተር ሱዛን ኮሊንስ (ፎቶ እኤአ 2015 ዋሽንግተን ፋይል)
ፎቶ ፋይል፦ በምርጫ ድምፅ አቆጣጠር ህግ ላይ ለውጥ እንዲኖር የሚያስችል ስምምነት ላይ መድረሳቸውን የገለጹት የዩናይትድ ስቴትስ ሁለቱ ዋና ዋና ፓርቲዎች እንደራሴዎች ቡድን መሪ የሆኑት የሜይን ዴሞክራት፣ ሴነተር ሱዛን ኮሊንስ (ፎቶ እኤአ 2015 ዋሽንግተን ፋይል)

የዩናይትድ ስቴትስ ሁለቱ ዋና ዋና ፓርቲዎች እንደራሴዎች በምርጫ ድምፅ አቆጣጠር ህግ ላይ ለውጥ እንዲኖር የሚያስችል ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ትናንት አስታውቀዋል።

የፕሬዚዳንታዊ ምጫዎችን ውጤት የሚያረጋግጠው ህግ የወጣው ከ150 ዓመታት በፊት ከእርስ በርስ ጦርነቱ በፊት እንደነበር ተነግሯል።

የህግ ረቂቁ ለውጥ ሀሳብ የመጣው ባለፈው የ2013 ዓ.ም. ጥቅምት መጨረሻ ላይ የተካሄደውን ምርጫ ውጤት ለመቀልበስ በወቅቱ ፕሬዚዳንት የነበሩት ዶናልድ ትራምፕ አድርገውታል በተባለው ጥረትና ታኅሣስ 28/2013 ዓ.ም. በምክር ቤቱ ላይ በተፈፀመው ጥቃትና ሁከት ላይ ከፍተኛ ምርመራ እየተካሄደ ባለበት ወቅት መሆኑ ነው።

ትናንት የቀረበው ጥናት ሁለት ገፅታ ያለውና ምርጫ የሚያስፈፅሙ የክፍለ ግዛቶችና የአካባቢ የምርጫ ባለሥልጣናትን ደኅንነት የሚያጠናክር አንቀፅ የተካተበት መሆኑ ተዘግቧል።

XS
SM
MD
LG