በ18ኛው የኦሬገን የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ በሴቶች 10 ሺህ ሜትር በለተሰንበት ግደይ የመጀመሪያ የወርቅ ሜዳሊያ አግኝታለች። በወንዶች ማራቶን የፍጻሜ ውድድር 2 ሰዓት ከ 5 ደቂቃ ከ 36 ሰከንድ በመግባት የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮንሺፕ ኢትዮጵያ ሁለተኛውን የወርቅ ሜዳሊያ በታምራት ቶላ አማካኝነት አግኝታለች። አትሌት ጎተይቶም ገብረስላሴ ለኢትዮጵያ ሦስተኛውን የወርቅ ሜዳሊያ አስገኘች።