የአፋር ክልል በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት ጉዳት በደረሰባቸው አካባቢዎች የሚገኙ ነዋሪዎችን እና ተፈናቃዮችን ለማገዝ የዕርዳታ አቅርቦት እጥረት እንዳለበት ገለፀ፡፡
የክልሉ የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ጽ/ቤት ለቪኦኤ በሰጠው ማብራሪያ፣ ለክልሉ ተረጂዎች እየደረሰ ያለው እርዳታ በብዛትና በጥራት አነስተኛ በመሆኑ፣ ዓለም አቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች ተገቢውን ምላሽ ካልሰጡ ከፍተኛ ጉዳት ሊደርስ እንደሚችል በመግለፅ አስጠንቅቋል፡፡
በክልሉ በጦርነቱ ምክንያት ተፈናቅለው ከነበሩት 336 ሺህ ሰዎች ውስጥ እስካሁን ድረስ ዘጠና ከመቶ የሚሆኑትን ወደ ቀዬያቸው እንደተመለሱ የተናገሩት የጽ/ቤቱ ኃላፊ “እነሱም ቢሆኑ በአካባቢያቸው የነበሩት የአገልግሎት መስጫ ተቋማት በመውደማቸው ትኩረት ይሻሉ” ብለዋል፡፡
/ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/