በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሰሜን ሸዋና ኦሮሞ ብሔረሰብ አዋሳኝ ቦታዎች በተቀሰቀሰ ግጭት ሕይወት ጠፋ


የኢትዮጵያ ካርታ
የኢትዮጵያ ካርታ

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ ግድም ወረዳ እና በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ጅሌ ጥሙጋ ወረደ አዋሳኝ ቦታዎች ትናንት በተቀሰቀሰው ግጭት ሰዎች መሞታቸው እና መቁሰላቸውን የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች ገለፁ።

ከሁለቱም አስተዳደር ዞኖች ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች ለግጭቱ መቀስቀስ የተለያዩ ምክኒያቶችን ሰጥተዋል።

አንደኛው ወገን መንግሥት ሸኔ እያለ የሚጠራውና በአሸባሪነት የተፈረጀው ታጣቂ ቡንድ ነው ሲል ሌላኛው ደግሞ የመንግሥትን ታጣቂዎች ተጠያቂ ያደርጋል። ከመንግሥት በኩል መረጃ ለማግኘት በተደጋጋሚ ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

/ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/

በሰሜን ሸዋና ኦሮሞ ብሔረሰብ አዋሳኝ ቦታዎች በተቀሰቀሰ ግጭት ሕይወት ጠፋ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:45 0:00

XS
SM
MD
LG