በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የደም እጥረት እና ብክነት በኢትዮጵያ 


የደም እጥረት እና ብክነት በኢትዮጵያ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:54 0:00

የደም እጥረት እና ብክነት በኢትዮጵያ

በኢትዮጵያ የደም አቅርቦት ችግር ሰፊ ነው፡፡ ከግማሽ ምዕተ አመት በላይ በቆየው የደም ልገሳ አቅርቦት ስርዓት ውስጥ፤ በየአመቱ የደም ፍላጎት በ 10 ከመቶ እያደገ እንደሚገኝ የብሔራዊ የደም ባንክ አስታውቋል፡፡ በተለይም የእናቶችና የጨቅላ ህጻናት ሕይወትን፣ እንዲሁም የትራፊክ አደጋ ተጎጂዎችን እና በጽኑ ህመም ላይ ለሚገኙ በሽተኞችን ሕይወት የሚቀጥለው ደም በህጻናት የሕክምና ክፍል ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ ይባክናል፡፡

ይህም ሃገሪቱ በግዢ የምታስገባቸው የደም ልገሳ መሰብሰቢያ ከረጢቶች በአዋቂ ልክ የተገዙ በመሆኑ እና አነስተኛ ደም ሊይዙ የሚችሉ የህጻናት የደም መለገሻ ከረጢቶች ባለመኖሩ መሆኑን ባለሞያዎች ይናገራሉ፡፡ በዚህ የተነሳም ለአንድ ጨቅላ ሕጻን በክብደቱ መሰረት ሊሰጥ የሚችል ከ 10 እስከ 40 ሚሊ ደም ለመስጠት ሲባል አንድ የ450 ሚሊ የደም ከረጢት እንደሚከፈትና ከተከፈተ በኋላም ለባክቴሪያ ስለሚጋለጥ አብላጫው እንደሚደፋ የአሜሪካ ድምጽ ያነጋገራቸው የጤና ባለሞያዎች ይገልጻሉ፡፡

ይህም ብቻ ሳይሆን ትናንሽ የደም ከረጢቶች አቅርቦት ኖሮ ቢሆን ኖሮ አንድ ሕጻን ከአንድ የደም ቦርሳ ከ3 እስከ 10 ጊዜ ሊጠቀም የሚችልበት ዕድልም መክሸፉንም ነው ባለሞያዎች የሚያስረዱት፡፡ የብሔራዊ የደም ባንክ በበኩሉ ያለፈን ዓመት በዚህ ዙሪያ ያለው ፍላጎት እና ክፍተት ምን ያህል መሆኑ ማጥናቱን በመግለጽ በቀጣይ አመት አነስተኛ የደም መቀበያ ከረጢቶችን ግዢ ለመፈጸም ተዘጋጅቼያለሁ ብሏል፡፡

/ዝርዝሩን ከተያያዘው የምስል ፋይል ይከታተሉ/

XS
SM
MD
LG