በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስ እና የቻይና ከፍተኛ ባለስልጣናት በሃገራቱ መሃል ያለውን ውጥረት ለማርገብ ዛሬ ተወያዩ


የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን ከቻይናው አቻቸው ዋንግ ዪ ጋር ፤ ብሊንከን በቀኝ በኩል
የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን ከቻይናው አቻቸው ዋንግ ዪ ጋር ፤ ብሊንከን በቀኝ በኩል

የዩናይትድ ስቴትስ እና የቻይና ከፍተኛ ባለስልጣናት በሁለቱ ሃገራት መሃከል ያለውን ውጥረት ለማርገብ ዛሬ ውይይት አድርገዋል። የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን ከቻይናው አቻቸው ዋንግ ዪ ጋር የቡድን ሃያ አባላት ስብስባ እንዳበቃ በኢንዶኔዥያ ባሊ ተገናኝተው ተወያይተዋል።

ከስብሰባው በፊት የውጭ ጉዳይ ሚኒትር አንተኒ ብሊንከን በዩናይትድ ስቴትስ እና በቻይና መሃከል ያለውን ውስብስብ እና የራሱ የሆነ ውጤት የሚያስከትል ግንኙነት ብዙ ሊወራበት ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።

የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ በበኩላቸው ቻይና እና ዩናይትድ ስቴትስ በትክክለኛው ጎዳና እንዲጓዙ በጋራ መስራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

ዩናይትድ ስቴትስ እና ቻይና፤ በቻይና በስተደቡብ የባህር በር እና ስልታዊ ቦታ በሆነቸው በታይዋን እንዲሁም በንግድ እና በሰብዓዊ መብት አያያዝ ሁኔታዎች አይስማሙም።

በዛሬው ዕለት ያደርጉት ስብሰባም የአየር ንብረት ለውጥን፣ አለም አቀፍ የጤና ስርዓትን፣ የጸረ ናርኮቲክ ውጊያዎችን እና በማይናማር ያለው ሁኔታ የሚዳሰሱ እንደሆኑ የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ዳንኤል ኪርትንብሪክ ተናግረዋል።

የብሊንከን እና የዋንግ የመጀመሪያው ስብስባ በሁለቱ ሃገራት የጋራ ግንኙነት ላይ የሚያተኩር ሲሆን ሁለተኛው ስብሰባቸው ደግሞ በቀጠናዊ እና አለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር እንደሆነ የዲፖሎማሲ ህትመቶች አስታውቀዋል።

XS
SM
MD
LG