በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሃጂ ተጓዦች በአነስተኛ ቁጥር በመካ ኢድ አል አድሃን አከበሩ


ሙስሊም ምእመናን በመካ 2014
ሙስሊም ምእመናን በመካ 2014

ከመላው አለም የተሰባሰቡ እና ዘንድሮ ቁጥራቸው እጅግ አነስተኛ የሆኑ የሃጅ ተጓዦች የኢድ አል አድሃ በዓልን ሴጣንን በመውገር አሳለፉ።

የመጀመሪያዋ ጀንበር ከወጣችበት ሰዓት አንስቶ በምዕራብ ሳዑዲ አረቢያ መካ አቅራቢያ ባለው ሚና በተሰኘ ቦታ አነስተኛ ቁጥር ያላቸው ምዕመናን ሶስት ማዕዘን በሆነው እና ሰይጣንን በሚወክለው የኮንክሪት ግንብ ላይ ድንጋይ ወርወረዋል። ይህም አብርሃም ልጁን እስማኤልን ሊሰዋ በተጓዘበት ወቅት ሰይጣን የአምላኩን ትዕዛዝ እንዳይቀበል ሶስት ጊዜ የተፈታተነውን ይወክላል።

ይህ ቦታም ባለፉት አመታት በቦታ መጣበብ ሳቢያ ከፍተኛ የሆነ መረጋገጥ የደረሰበት አካባቢ ነበር። በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ ከአምስቱ ማእዘኖች አንዱ የሆነው እና ሙስሊሞች ቢያንስ በሕይወት ዘመናቸው አንዴ ሃጂን ጉዞ እንዲያደርጉ በሚያዘው ትዕዛዝ መሰረት ይሄ ወቅት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሙስሊሞች የሚሰባሰቡበት ነበር።

እ.ኤ.አ በ2019 ዓ.ም 2.5 ሚሊየን ሙስሊሞች ይሄንን ጉዞ ተካፍለዋል። ይሁን እንጂ ከዛ በኋላ ባሉት አመታት ሳዑዲ አረቢያ የኮቪድ 19 ስርጭትን ለመቆጣጠር በምታደርገው ጥረት የተነሳ የተጓዦች ቁጥር ላይ ገደብ በመጣሏ ምክንያት የተጓዦች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ የቀነሰ ሲሆን በዚህ ዓመት አንድ ሚሊየን ሙሉ ለሙሉ የኮቪድ 19 ክትባት የወሰዱ ሙስሊሞች ብቻ ተገኝተዋል። ከእነዚህ ውስጥም 780,000 ያህሉ የውጭ ሃገር ዜጎች ናቸው።

የሃጅ እና ኡምራ ጉዞ እስከ 5000 ዶላር የሚያወጣ ሲሆን በደህና ወቅት ሳዑዲ አረቢያ እስከ 12 ሚሊየን ዶላር ድረስ ገቢ የምታገኝበት ወቅት ነበር።

XS
SM
MD
LG