በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ ውስጥ ተይዘው የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች አሁንም ችግር ላይ መሆናቸውን ገለፁ


ፎቶ ፋይል፦ ሰመራ፣ አፋር
ፎቶ ፋይል፦ ሰመራ፣ አፋር

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን “ህገወጥና የዘፈቀደ እሥራት” ሲል በጠራው ሁኔታ በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ ውስጥ ተይዘው የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች አሁንም በበረታው የወቅቱ ሞቃት የአየር ጠባይና በበሽታ ምክንያት እናቶችና ህፃናት እየታመሙ መሆናቸውንና የሰዎች ሞትም መቀጠሉን ለቪኦኤ ገልፀዋል።

ይኖሩበት ወደ ነበረው አካባቢ እንዲመለሱ እንዲደረግም ጠይቀዋል።

በሌላ በኩል “የትግራይ ክልላዊ መንግሥት የውጭ ግንኙነት ፅህፈት ቤት” መሆኑን የሚናገረው ቢሮ በመላ ሃገሪቱ “በማንነታቸው ምክንያት በጭካኔ ተይዘዋል” ሲል የገለፃቸውና “በአሥር ሺሆች የሚቆጠሩ” ያላቸው የትግራይ ተወላጆች እንዲፈቱ ዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ጫና እንዲያደርግ ጥሪ አድርጓል።

የፌዴራልና የክልል ባለሥልጣናትን ምላሽ ለማካተት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው ባይሳካም የአፋር ክልል መንግሥት ባለሥልጣናት በቅርቡ ሰጥተዋቸው የነበሩ አስተያየቶችንና የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ያወጣውን መግለጫዎች መልዕክት አካትቶ የትግርኛ ዝግጅት ክፍላችን ባልደረባ ገብረ ገብረመድህን ያጠናቀረውን ሪፖርት ቆንጂት ታየ ታቀርበዋለች።

ሙሉውን ከተያያዘው ዘገባ ያዳምጡ።

please wait

No media source currently available

0:00 0:06:34 0:00

XS
SM
MD
LG